ስለእናንተ እኛ እናፍራለን ❗️


ስለእናንተ እኛ እናፍራለን ❗️

ሃሰን ዋሬ ነስሪ
ታህሳስ 24/04/2013 ዓ.ም

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ታላቋን ሶማሌ የመደራጀት ህልም በብልግና ድርጅታዊ መዋቅርነት ተሻግሮ መንፈስ ሆኗል፡፡ መንፈሱ ታሪክን እንደ ፖለቲካ ርዕዮት ከማየት የሚጀምር ሲሆን፤ ታሪክ ላይ መቸንከር ዋና መገለጫው ነው፡፡ በእኩልነት የመቆም ፍርሃት ያለበት የተለቁዋ ሶማሌነት ህልም  መንፈስ በእኩል እድል ሳይሆን በእኩል ውጤትና ብልጫ አስተሳሰብ መመራትን ይፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ራሱን ለማየትና ለማግኘት የሚቸገረው ይህ ኃይል፣ ከ ቤተ-ኢትዮጵያ ይልቅ ታላቁን ሶማሌ ህልምን መደበቂያ ምሽጉ ነው። ኢትዮጵያዊነትን በሌሎች የተጫነ አድርጎ የሚያቀርበው የአስተሳሰቡ ተሸካሚ ኃይል፣ መሠረት በሌለውና በተጋነነ ጥላቻ ሌላውን ለማጥቃት አልፎም ለመዋጥ ሲያደባ ውሎ ያድራል፡፡ ትላንትና ያልነበረውን ጥያቄ አሁን እየወለደ፣ ዛሬ የሌለውን ጥያቄ ለነገ እያማጠ እንደሚሄድ ከልምድ አይተነዋል፡፡

መንፈሱ የተጣባቸው የሶማሌ ጥምር ኃይሎች የፖለቲካ መርህ አልባነት፣ ይሉኝታ ቢስነትና የሞራል ዝቅጠት መገለጫቸው ሆኗል፡፡ ይህ በመንግሥታዊ መዋቅሩ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ ያለ አመለካከት በየመድረኩና በየሚዲያው ሲገለጥ ከርሟል፡፡ ሦስት ዓመት ሙሉ የታዘብነውን ነውር በአክቲቪስት ሙስጠፋ መሀመድ አረዳድ ‹የሴራ ፖለቲካ› ተብሎ ይጠራል፡፡ ለሌላው ነውር የሆነው ለዚህ ኃይል ‹ሴራ› የሚል ስያሜ አለው፡፡ የመንፈሱ አውራሾች ከጀርባ ሆነው በጫኑት/በሚጭኑት አስተሳሰብ ሀገር በህልውና ፈተና ላይ ወድቃ እንኳ የአስተሳሰቡ ተሸካሚዎች ታውቆ ባደረው የመርህ አልባነት፣ ይሉኝታ ቢስነትና የሞራል ዝቅጠታቸው እንደቀጠሉ ነው፡፡

የሰሜን ዕዝ በከሃዲውና ጨፍጫፊው ትህነግ ጁንታ  ከጀርባ መወጋቱን ተከትሎ በተጀመረው ጦርነት እንደ ሀገር ሳይሆን እንደጠባብ የፖለቲካ ቡድን ጥቅሙን እያሰላ ‹ከዚህ ጦርነት ምን እናተርፋለን› በሚል ሴራ ሲጎነጉን ሰንብቷል፡፡ ሀገር በህልውና ፈተና ላይ ወድቃ፣ የሀገሪቱ 70 ከመቶ መካናይዝድ የጦር መሳሪያ ተዘርፎ፤ 45 ከመቶ የሚሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ተከፍቶ፤ ‹ሁሉም ነገር ወደ ሕግ ማስከበር› በተባለበት ሰዓት የታላቋን የሶማሌዎች ጥምር አስተሳሰብ ተሸካሚው የሽብር ቡድን የግዛት መስፋፋት ቅዠት ላይ ተጠምደው   ከጦርነቱ በኋላ ገደማይቱን ኡንደፎኦንና አደይቱን ከአፋር ግዛትነት አላቆ በሶማማ የግዛት ቁጥጥር ለማድረግ የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ ጥቃት እያደረሱ በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ያለውን የአፋር ልዩ ሀይልን እየወነጀለ የጦርነት መግለጫ እያወጣ የግዛት መስፋፋት ላይ የስለሚቻልበት ሁኔታ ነገር ያብሰለስል፣ ሴራ ይቀይስ፣ ኃይል ያሰባስብ፣… ነበር፡፡

ስለ አካባቢዎች የቀደመ ማንነት ታሪክ የተዛባ የሚዲያ ዘገባ በማሰራት፣ በአካባቢዎቹ በሶማሌ ክልል ውስጥ ያለ ለማስመሰል ለነሱ ፍላጎት ተገዥ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን ከአገር ውስጥና ከዲያስፖራው በማፈላለግ የገጽ ለገጽ ግንኙነት ለመፍጠር በመሞከር፣ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የተጠኑና ተጨማሪ ቅራኔዎችን የሚፈለፍሉ አጀንዳዎችን በመልቀቅ እንዲሁም የሶስቱም ሶማሌዎች አመራሮችን በጉዳዩ ዙሪያ በመወትወት  የኀይል እና የትጥቅ  ማሰባሰብ ስራ ስሰራ ሰንብቷል፡፡

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያው አፋር ክልል የፈፀመው ትንኮሳ በማስመሰል የወጣው የጦርነት ጥር የቀረበውም ‹የርስት› ጉዳይ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ‹በመርህ› ስም እስከ ማንሳት ተደርሷል፡፡ ባሰበው ልክ ኃይሉ ያሰባሰበውን ጥቃት እና ህልሙን ባያሳካለትም በጁንታው እግር አፋር ላይ እጁን ያስረዘመ በመሆኑ በመርህ ስም በሶስት ቀበሌዎችን ወደ ራሱ ግዘት የመመለስ የዓላማውን የአፋር ሕዝብ ከግዛታቸው ለመፈናቀል እና ህልሙን ለማሳከት መንግስት እያደረገ ያለውን ሀገርን የመዳን ስራ  ለማደናቀፍ የማያውቅበትን የመርህ ፖለቲካ መሟገቻ አድርጎ ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡

አካታችና አሰባሳቢ የፖለቲካ አካሄድ የሚፈልጉ የሶማሌ ፖለቲከኞች ቢኖሩም የዝያድባሬ ታላቋን የሶማላዊያን የመመስረት እና የመገንጠል የግዛት መስፋፋት መንፈስ ተጠቂ የሆኑ አመራሮች የያዙት መንገድ ለተከበረው የሶማሌ ሕዝብም ሆነ ለመላ የኢትዮጵያውያን አደጋ ያዘለ ሆኖ ይታያል፡፡

የኦጋዴን አስተሳሰብ ተሸካሚው ኃይል፣ በቀጣይ ኢትዮ-ጅቡቲ መስመሩን ለመቆጣጠር እና ወዳ ሶማሌ ክልል የመጠቅለል ህልምና በአቶ ማህሙድ ዲርር እና የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ-ጉባኤ በአቶ አዳም ፋራህ የሚማረው የኢሳ ብሄረሰብ ክልል በአፋር ለመመስረት እንድያስችል የኢሳ ብሄረሰብ ፓርቲ እስከማቋቋም የሚደርስ የማታገያ ስልት የቀየሰ ቢሆንም በቆፈረው ጉድጓድ ራሱ እንደሚገባበት ስንናገር የቀድሞው የነፍሰ የትህነግ ጁንታውን  የውድቀትና ለውርደት እንጂ ዕውን የማይሆን መሆኑን ከፈጠረያችሁ ከተፈጠፊያችሁ ከትህነግ ጁንታው መማር ያስፈልጋል፡፡

አፋር የሚፈልጋት ኢትዮጵያ፤ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ እና በህግ-ገዥነት የተመሠረተ ዴሞክራሲ የሰፈነባት ጠንካራ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ያላት አገር ተገንብታ ማየት ነው፡፡ ፖለቲካ የሕዝብን ስትራቴጅክ ጥቅም ለይቶ መታገል ነውና ይህን ቀናዒ ፍላጎቱን በመደገፍ ሶማሌው፣ አፋሩ፣ ሲዳማው፣ ጉራጌው፣ ጋሞው፣… ከኦገዴነዊና የታላቋን ሶማሊያም የኢሳ ብሄረሰብ ክልልን በአፋር የመመስረት ተፈላጊውን አስተሳሰብ ተሸካሚነት ነጻ የሆኑ የሶማሌ ፖለቲከኞች አብረውት ይሰለፋሉ፡፡ ግፍን የሚቃወም ሁሉ በቤቱ እየተገደለ እየተገፋ ያለውን ከአፋር ጋር አብሮ ይሰለፋል!

በቅጄት  የፈረሰ ሀገር እንጅ የተገነባ ሀገር የለም!!
በሶስት ቀበሌዎች ስም የሚደረግ የግዛት መስፋፋት የተዘጋ ፋይል ነው!!

Leave a comment