የወራሪው ፕ/ት ሲያድ በሬ አደራ ያለባውቸ ኢሳ ና የአርገር ወዳዱ የአፋር ህዝብ  ታሪክና የመንግስት ጠልቃ ገብነት በአጭሩ!

===============================
===============================
*አፋር ና ወራሪው ኢሳ ማን ና ማን ናቸው?
*የግጭታቸው መንስኤስ ምንድነው?
*አፋር ከጥንት ጀምሮ አገራችንን ከወራሪወች ለመጠበቅ ምን ያህል መስእዋትትነ ከፍሏል?
*የአሁኑ ወራሪው እሳ ህልማቸው ምንድነው?
ለማንም የኢትዮጵያዉ አድስ የሆነ ታሪክ ባይኖረኝም ካለንበት የግዜ ሁኔታ አንፃር ትንሽ ለማብራራት እሞክራለሁኝ ።
የአፋር ህዝብ ለእናቸው ኢትዮጵያ የሚገባቸውን መፅዋእትነት የከፈሉ መሆናቸው ለሁሉም የኢትዮጵያዊ አድስ ታሪክ አይደለም።
ለምሳሌ ያህል፦
1=የፖርቱጋል
2=የኢጣልያ
3=የእንግሊዝ
4=የግሪክ
5=የፈረንሳይ
6=የቱርክ
7=የግብፅ ወ.ዘ.ተ……. አገራት ወራሪዎችን በአፋር ምድር አርገው ኢትዮጵያን የመውረር ህልማቸው ሳይሳካ እንድቀር የአፋር ህዝብ የከፈለው መፅዋእትነት በማንም ኢትዮጵያዊ ልብ በማይደመሰስ ፅሁፍ የተፃፈ ታሪክ ነው!
ዛሬም እንደቀጠለ ነው!
*የሲያድ በሬ የረጅም ጊዜ ህምል አደራ ያለባቸው ኢሳዎችስ ማን ናቸው?
♦መፍትሄ አልባው የኢሳና አፋር ግጭት ከዘመነ መገንጠል
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ እስከ ዘመነ መደመር።
~~~~~~~~~~~
የዚያድ ባሬ ስተራተጂ አስፈጻሚዎች በሶማሊ ክልል በኩል የአፋር መሬትን መያዝ የሚፍልጉት ለምንድነው ?

የዚያድ ባሬ ታላቋ ሶማሌ እዉን ማድረግ በወቅቱ ባይሳካም አሁንም በተለየዩ መንገድ ሶማሌዎች በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ተጽዕኖ ፈጣሪ የመሆን ፈላጎታቸው አልጠፋም።

እንደሚታወቀው ይህንን ለማድረግ ዋና አላማቸው ኢትዮጲያን ማዳከም እንደሆነ በግልጽ ይታያል።
ስለዚህ በቀጠናው በተለይ ለኢትዮጺያ የባህር በር መግብያና መውጫ የሆኑ ቦታዎችን መያዝ የሶማሌዎች ዋና የረጅም ጊዜ ዕቅዳቸው ነው።
ከ17ተኛ ክፍለ ዘመን በፊት እንደጀመረ የሚገመተውና መፍትሄ አልባ የሆነው የኢሳና አፋሮች ግጭት የዚህ አካል ስለመሆኑ በብዙ ማስረጃዎች በማስደገፍ መናገር ይቻላል።

የኢሳ ሶማሌዎች በታሪክም ቢሆን በጀቡቲም ሆነ በኢትዮጲያ እንዳልነበሩ በቅርቡ ዶ/ር በለጠ በላቸው ይሁን በፃፉት ‘’ጀቡቲ የጥገኝነታችን መስፈሪያ’’ በተሰኘ መጽሀፋቸው በደንብ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ከዚህ ረጅም ዘመናት በሓላ የውጪ ወራሪ ሃይሎች ወደ ምስራቅ አፍሪካ መምጣት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ኢሳዎች አፋሮችን ከወራሪዎች ጋር በመሆን እያጠቁ እንደመጡ በብዙ የታሪክ ምሁራን ይነገራል።

የኢሳ ሶማሌዎችም ሆነ አፋሮች ሁለቱም በአብዛኛው የአርብቶ አደር ኑሮ መሰረት ያደረጉ ስለሆኑ ለዘመናት በእነሱ መሃል የሚፈጠረው ጦርነት ሁሉ በዉሃና በግጦሽ የሚነሱ ግጭቶች በማለት አሳንሶ ማየትና ተገቢ የሆነ ትኩረት አለማገኘቱ ችግሩ እንዳይፈታ ካደረጉ ነገሮች አንዱ ነው።
ምንም እንኳ በየጊዜው የሚጋጩት አርብቶ አደሮች ቢሆኑም በተለይ የኢሳዎች የመሬት ማስፋፋት አካሄድ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ድብቅ አላማ ባላቸው ፖለቲከኞች የሚመራ መሆኑ ጉዳዩን ቀረብ ብሎ ላየ ግልጽ ነው።

በንጉሰ ነግስቱ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት በሶማሌ ኢሳዎችና አፋሮች መሃል ሲደረጉ የነበሩ ግጭቶች እና ሽምግልናዎች የሚያሳዩ ማስረጃዎች ላይ እንደተገለጸው በየጊዜው የሚደረጉ ስምምነቶችን አፍርሶ የተገኙት ኢሳዎች ነበሩ። ይሄም እስካሁን በማስረጃ ተቀምጧል።

በነገራችን ላይ አሁን ኢሳዎች የእኛ መሬት ነው እያሉ ያሉት በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የኢሳ-ሶማሌዎችና አፋሮች የግጦሽ ክልል ወሰን ከነበረበት 447 ኪ/ሜ ወደ አሁኑ የአፋር ክልል ገብቶ ነው።
የአሁኑ የኢሳ እና የአፋር ጉዳይ ከድሮ ለየት የሚያደርገው ግን ከግጦሽ ክልልነት ወደ አስተዳደር ክልልነት ከፍ ያለ የፖለቲካ ጥያቄ ለታላቋ ሶማሌ ህልም ማሳኪያ የሚደረግ የመሬት ማስፋፋት ነው።
የኢሳ ሶማሌ ጎሳዎች በህግ፣ በታሪክና በዕውቀት አያምኑም።

ብዙ ጊዜ በብዙ ምሁራኖችና የሀገር ሽማግለዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ካሁን በሗላ ይህ ግጭት ማብቃት አለበት በማለት ለመነጋገር ተሞክሯል። በቁርዓን ሳይቀር ማሃላ ተፈጽሟል።
ይህም ኢሳዎች ብግልጽ እንደሚሉት በባህላቸው በሃይል መውሰድ እስከቻሉ ድረስ የማንም መሬት የእነሱ መሬት ይሆናል የሚል ባህላዊ ህግ እንዳላቸው ይናገራሉ ።

በየመንስታቱ የተለየያዩ አጀንዳዎች ቢቀያየሩም የኢሳዎች ዋና ህልም ግን አንድ መዳረሻ ነው።
እሱም በአዋሽ ወንዝ ዳርቻና በሌሎች የአፋር ክልል ስተራተጂክ የሆኑ መሬቶችን በብቼኝነት መቆጣጠር።
ለምሳሌ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ከነበሩበት አከባቢ በጣም ገፍቶ በመግባት በተለይ በደርግ ጊዜ በነበረው ጦርነት ውስጥ ብዙ የአፋር መሬቶች ይዘዋል።
እንዲያዉም ኢሳዎች በደርግ ጊዜ በጣም ወደ አፋር እየገቡ ሲመጡ የወታደራዊ መንግስት አንድ አዋጅ አውጆ እንደነብረ ይነገራል።

እሳዎች ከመንገዱ 50 ኪ/ሜ ወደ አፋር መሬት ገብቶ ከተገኙ በወታደር እርምጃ እንዲወሰድባቸው ታውጆ እንደነበረም ይታወቃል።
የደርግ መንግስት ወድቆ የወያነ መንግስት ሲገባ ኢሳዎች አሁንም የመሬት ወረራ አካሀዱ።
ለኢህአዴግ መንግስት አቤት ቢባልም በጊዜው የኤርትራ ጦርነት እንደ ምክንያት ተነግሮ የአፋር ጥያቄ ሰሚ አጣ።

ጦርነቱ ካበቃ በኃላ ግን የወያነ መንግስት ከጀቡቲ ጋር ባደረገው የወደብ ስምምነት ጋር በተያያዘ ኢሳዎችና የወያነ ጀኔራሎች በዛ አከባቢ ሲፈልጉ ጦርነት፣ ሲፈልጉ ሌብነት፣ ሲፈልጉ ደግሞ እርቅ እየፈጸሙ የኮንትሮባድ ቀጠና አደረጉት።
እስካሁኑ ግጭት የነበረው ሁኔታ ይህን ይመስላል።
ባለፉት 28 አመታት ከወያነ ጋር በመሆን በእነ አባይ ጸሃዬ ወሳኝነት 3 ቦታዎች ልዩ ቀበሌ ተብሎ እንዲሰጣቸው ደረጓል።

እነዚህ ከተሞች ጋዳማይቱ፣ ኡንዳፎዖ እና አዳይቱ የሚባሉ ሲሆኑ ለ28 አመታት አንድ አፋር እዛ አከባቢ በሰላም እንዳይንቀሳቀስ፣ በሰላም እንዳይኖር የሽብር ቀጠና ተደርጎ በሌላ በኩል ደግሞ የአፋር ህዝብ እራሱን እና መሬቱን እንዳይከላከል በሪሞት እያስተዳደሩ እዚህ ላይ ተደርሷል።
አሁን ደግሞ አራተኛው የመንግስት ለውጥ ላይ ደርሰናልና ኢሳዎች በዚህ ሁኔታ የያዙትን መሬቶች ወደ ሶማሌ ይካለሉልን እያሉ ያሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ባለፉት አመታት ከወያነ ጋር በመሆን በእነ አባይ ጸሃዬ ወሳኝነት እነዚህ ቦታዎች ልዩ ቀበሌ ተብሎ እንዲሰጣቸው ደረጓል።
ይሁን እንንጂ ይህንን ውሳኔ በአፋር ህዝብ ዘንድ ምንም አይነት ተቀባይነት የለዉም። እንዲያዉም የኢትዮጲያ መንግስት ጉዳዩን በገለልተኛ አካል አጥንቶ ኢሳዎች በሃይል የያዙት የአፋር መሬቶች ሊያስማልስ ይገባል።

አሁን በሀግራችን ያለው ሁኔታ የለውጥ ባህሪ ነው እየተባለ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ይገኛል።
ከልቡ በኢትዮጲያዊነት የምያምን ሁሉ ስጋት ውስጥ ይገኛል።
ከብሔሮች ከፍ ብሎ ኢትዮጲያዊነት የሚል መሪ በተገኘበት፣ ከኢትዮጲያ ከፍ ብሎ አፍርካ በሚንልበት በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሃይሎች ውስጥ እንኳ ይህንን ችግር እንዳይፈታ የሚሰሩ ሰዎች አሉ።
የአሁኑ ኢሳና የአፋር ግጭትም ለአሁኑ የኢትዮጲያ ሁኔታ ተጨማሪ ፈተና እንዲሆን ተደርጎ በሰልጠና እና በሎጂስትክ ተደግፎ የተዘጋጀ እንደሆነ በጣም እርግጠኛ በሆን የአፋር ህዘብ በማስረጃ ደግፎ የሶስት ሀገረ ጠልቃ ገብነት እንደለ ለማዕከላዊ መንግስት በተደጋጋሚ አቅረበዋል ።

ስለዚህ መንግስት አዲስ አበባ ላይ በሚቀርበለት ሪፖርት ብቻ ሳይሆን የተለየ ትኩረት በመስጠት ጉዳዩን ማርገብ ሳይሆን ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አለበት።
የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እዛ አከባቢ ላይ እንዳይሰፍር የሚያደርጉ የኦጋደን ነጻ አውጪ ግንባርና አልሸባብ የኢስመኤል ኡመር ጌለ የጀቡቲ ሀይሎች ና ሌሎች ታጣቂዎችን የፌደራል መንግስት ማስቆም አለበት።

ልዩ ሃይሉ ያልተመጣጠነ እርምጃ ይወስዳል ለሚለው ክስ የፌደራል መንግስት ልዩ ሃይሉ ከአከባቢው ሳይወጣ በቅንጅት ሊሰሩ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከአፋር ክልል መንግስት ጋር መምከር ነበረበት ።
ከዚህ ዉጭ ግን በአፋር ክልል ለሚገኙ ኢሳዎች ጉዳይ ላይ የሶማሌ ክልል መንግስት የሚሳተፍበት ምክንያት ግልጽ መሆን አለበት።

ኢሳዎች እንደማንም ዜጋ በሰላም መኖር ካለባቸው የአፋር ክልል መንግስትና የፌደራል መንግስት ብቻ ሊመለከተው ይገባል።
ግልጽ ያልሆኑ ከጀቡቲ እስከ ዲሬ ዳዋ እንዲሁም ጂጂጋ የሚደረጉ ውይይቶች የህዝብን ጥርጣረ ከመጨመር ዉጭ ምንም ውጤት እንደሚያመጡ ማዕከላዊ መንግስት መገንዘብ ይኖርበታል ።

“”ሌለኛው የሶማሌ ክልል የጦርነት አዋጅና የጎንዮሽ ምልከታዎች “””
በጅቡቲ ከ85% በላይ የአፋር መሆኑ ይታወቃል።በታሪክ አጋጣሚና በሶማሊያን የማይወደደው የኢሳ ጎሳ በሶማሊያ ምድር ጭራሽ እንዳይኖር ሲባረር ይሸሸግበት ቦታ ይመረኮዝበት በትር ያጣው ተሳዳጁ ኢሳ ወደ ጅቡቲ በመፈርጠጥ ተለሳልሶና ተመሳስሎ ለተወሰነ ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ የአፋሮችን የዋህነትና ደግነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በስውር ሃይሉን በማደራጀት የመንግስትነትን ስልጣን ለብቻው በመቆጣጠር ለበርካታ አመታት የአፋርን ህዝብ በሃገራቸውና በመሬታቸው ባይተዋር ሊያደርጋቸው ችሏል።

ይህ የኢሳ የመስፋፋት አባዜና በጅቡቲ አፋሮች ላይ የሚያደርሰው ግፍና እንግልት ከእለት ወደ እለት እየከፋ በመምጣቱ የአፋር ህዝብ ለመብቱ ለመታገል ከምንጊዜውም በበለጠ መልኩ እየተንቀሳቀስ ይገኛል።

ይህ ትግል ተጠናክሮ ከቀጠለ ለዘመናት በጅቡቲ የተንሰራፋውን የኢሳ የግፍ የአገዛዝ ስልጣን እንደሚያከትም ሙስጠፋም የሶማሊያ ክልል ምክር ቤትና ሰይጣንም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ይህ የአፋሮች የትግል እንቅስቃሴ እንቅልፍ እያሳጣቸው ቀንም ለሊትም እንዲቃዡ አድርጔቸዋል።ይህ የህዝብ ትግል እንደቀድሞው በቀላሉ የሚኮላሽ አለመሆኑን ሲረዱ በአፋር ትርያንግል ውስጥ የሚገኙ አካባቢዋችን ሰላምን ማደፍረስ ቀዳሚ ተግባራቸው መሆን እንደሚገባው እና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ትንኮሳዎችንና ግጭቶችን ፈጥረዋል።

የአሁኑ የእነ ሙስጠፋ ውሳኔም የዚሁ አካል የሆነና እንዱፎ፣ ገዳማይቱና አዳይቱ አካባቢዎች የሶማሊያ ናቸው የሚል ጭፍን ሃሰትን በመነዛት በተለይ በጅቡቲ የሚገኙ አፋሮች የሚያነሱትን የመብትና የዴሞክራሲያዊ እኩልነትና ፍትሃዊነት እንቅስቃሴ አቅጣጫ ለማስቀየር ከኢሳዊነት ድጋፍ አንዱ መሆኑን መገንዘብ የግድ ይላል።

የአማራ አርሶ አደሮች የአፋር አርብቶ አደሮችበድርቅ ጊዜና በግጦሽ መመናመን ምክንያት በተለያዩ ወቅቶች ማንም ፈቃጅና ከልካይ ሳያስፈልጋቸው አንዱ ወደ አንዱ ክልል እየገቡ በሰላምና በፍቅር ከቆዩ በኋላ ተሸኛኝተው ወደመጡበት ይመለሳሉ። አንደኛቸውም በግጦሽ የተጠቀሙበትን መሬት የእኔ ነው የሚል የተስፋፊነት ስሜት አሳይተው አያውቁም።(አልፎ አልፎ በግል አለመግባባት ከሚፈጠሩ ቀላል ጸቦች በስተቀር)

ኢሳ ሽንቱን የሸናበትን፣ ያነጠሰበትን፣ እንቅፋት የመታበትን አካባቢ እያስታወሰ የእኔ ነው ማለት ከፍጥረቱ ጀምሮ።የተጠናወተው ሰይጣናዊ ባህርይው ነው።

የአፋር ህዝብ የዚህ የእነሙስጣፌ ቀጥተኛ ሰለባ ገፈት ቀማሽ ሊሆን ይችላል።ነገ ግን ማንኛውም የገቢና የወጭ የንግድ እንቅስቃሴ የሚወሰነው በጅቡቲ የኢሳ መንግስት ፣በሶማሊያ ክልል መንግስት፣ በአልሸባብ ስለሚሆን ዛሬ እንደቀላል የምናየው የእነ መስጠፋ ውሳኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ የሞትና የህይዎት ጉዳይ መሆኑን ይበልጥ መረዳት ይገባናል።
ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ አቅልለን የምናየው ጉዳይ “”ቁጭ ብለን የሰቀለነውን ቆመን ለማወርድ የማይቻል አድርገነው”” ታሪክና ዘመንን እየረገምን እንዳንኖር አሁኑኑ በህብረትና በአንድነት ሆነን እየተካሄደ ያለውን” ጸብ ያለሽ በዳቦ” ማስቆም ይኖርብናል።

ሌለው እነዚህ ሦስት ቀበሌዎችን ፀጥታ ለማስከበር የክልሉን ሀይል አስወጥቶ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያሰማራ ብሆንም ሀገሪቱ የወጭና ገቢ የሆነው መንገድ ላይ በተደጋጋሚ የሚደረገው የሽብር ጥቂት ከወትሮው በተለየ መንገድ ዜጎች በሠላም ወቶ መግባት አልቻሉም ።

የመከላከያ ሰራዊት የዜጎችን ሰላም ከማስከበር ይልቅ የኮንትሮባንድ ስራውን በስራት አሸባሪዎች ጋር የጥቅም ግንኘነት በመመስረት የአፋር ህዘብ ህይወት እየተከተፈ ዝምታ የመረጠበት ምክንያት ግልፅ ባለመሆኑ የአፋር ህዝብ በመከላከያ ሰራዊት ላይ እምነት እንድያጣ አድርጎታል ።

መንግስት የሀገር ሉአላዊነትን የማስከበርም ሆነ ዜጎችን ከአሸባሪዎች ጥቃት መጠበቅ አመቻሉ ብቻ ሳይሆን ሥራው እንዳሰራ እያስጓጎለ ይገኛል።
የአፋር ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና የሀገሪቱን አንድነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው ተጋድሎ በመንግሥት በኩል እንቅፋት መግጠሙ በብዙዎቹ ዘንድ አስገራሚ ሆኗል፣ ግራ መጋባትም ፈጥሯል።

የአፋር ህዝብ አርበኝነት ትግል በመንግሥት የተደናቀፈበት ምከንያት የአማርኛ ቋንቋ የቃላት ፍች እንዳይሆን ስጋት አለኝ። ህዝብን የማዳን (ደህንነት መጠበቅ) ሥራ በመስራት ላይ ነን ስንል፣ ህዝብን የማደን (አደጋ ለመጣል መዋከብ) ሥራ መስሎአቸው ይሆን? አተረጓገም ላይ የተፈጠረው ያለመረዳዳት ችግር ከሆነ ይስተካከላል እንጂ ችግር የለውም። መንግሥት ሆን ብሎ ሽብርተኞችን የሚደገፍ ተግባር ላይ ተሰማርቶ ከሆነ ግን ይሄ አደገኛ አዝማሚያ ነው።
ዋና መንገዱን ከሽብርተኞች ለመጠበቅ የተሰማራው መከላከያን የሚመሩ የጦር ጀነራሎች ከሽብርተኞችና ኮንትሮባንድስቶች ጋር የጥቅም ግንኘነት በመፍጠር የሀገር ሉአላዊነት ከማጠበቅ ይልቅ ጥቅምን የማሳደድ ሥራ ላይ አትኩሯል።
አሁን በሚታየው ሁኔታ የፌዴራል መንግስት በዚህ መስመር ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ ግዲያ ማስቆም አልቻለም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአካባቢው ከሠፈረው ጦር በብዛት በመስመሩ በሚደረገው የህገወጥ ንግድ የጥቅም ተካፋይ በመሆኑ ለጉዳዩ ለዘብተኛ አቋም የሚያዙ ምስጢር ይሄው ነው። ሠራዊቱ እነዚህን ወንበዴዎች እገቡበበት ድረስ ገብቶ ስርዓት ማስያዝ ስገባው ከኮንትሮባንድ ጥቅም ስላገኘ ብቻ በአደባባይ የሚገደለው የንፁሃን የአፋር ልጆች ሞት ከቶም ምንም ሳይሰማው እነሆ ዜጎች በመንገድ እየተሸበሩ ካለምንም ጥፋታቸው የሞት ፅዋ እየቀመሱ ነው።

አሁን ምርጫው አንድ ብቻ ነው። እሱም መከላከያ የመንገድ ደህንነት መጠበቅ ባለመቻሉ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወደቦታው የፀጥታ ሐይሎች ወደቦታው መመለስ አሊያም በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ሞትና ሽብር ከአካባቢው የአፋር ፀጥታ ሐይሎችን ያስወጣው የፌዴራል መከላከያ ሠራዊት ለሚደርሰው ጥፋት ሐላፊነቱን እንዲወስድ በማድረግ ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ።

ከሁለቱ አንድ መሳካት የማይቻል ከሆነ ግን የአፋር ህዝብ በወንበዴዎች የሚደርስበትን ሞት በፌዴራል መከላከያ እምነቱን ጥሎ ከመቀመጥ ይልቅ መብቱን የሚያስከብርበት እርምጃ ራሱን ለመከላከል ስል የሚወስድበት ሂደቶች ቀይሶ መንቀሳቀሱ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

~አገራችንን ከወራሪ የመጠበቅ አገራዊ ግዴታችንን እንወጣ!!!! (ድል ለአፋር ህዝብ )

መከላከያ የአፋር ጣላት ነው።

መከላከያ የአፋር ጣላት ነው።

አድሱ የሶማሌ ክልል ፕረዘደንት አክቲቪስት አቶ ሙስጠፋ የክልሉን መሪነት በሶሻል ሚዲያ በኩል ከጨበጠበት ዕለት አንስቶ በአፋር ክልል ገዳማይቱ፣ ኡንደፎኦ እና አዳይቱ ቀበሌዎች በተለያዩ የውጭ ኃይሎች ቅስቀሳ ገንዘብ እና የጦር መሣሪያ በመበተን የአከባቢውን ስላምና እና ጸጥታ በመረበሹ ምክንያት በአከባቢው የመከላከያ ሠራዊት የህዝቡንና የመንገዱን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅና በአከባቢው ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ኃይሎችን ተከታትሎ ለህግ ለማቅረብ በአከባቢው መሠማራታቸው የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በአከባቢው የሰላም እጦት ችግር ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰና የሀገሪቱ የገቢና ወጭ ንግድ መተላለፊያ መስመር በሽብር እየተናጠ ባለበት ከዚያም አልፎ አሻባሪዎች ከወራሪዎች ተደምረው በከተሞችም ጭምር የሰው ህይወት በየዕለቱ በሚቀጥፉበት በአሁኑ ወቅት በህግ የተሰጠውን የመንገዱን ስላምና ድህንነት ማስከበሩን ትቶ በሌሎች የአፋር አከባቢዎች በሰላም የሚኖረውን ህዝቦችንን ሰላም ለማወክ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የአፋር ህዝብ በተለያዩ ግዜያት መከላከያ የመንገዱን ሰላም ለማስከበር ባለመቻሉ እና ከኮንትሮባንድስቶች ጋር ተመሣጥረው በየ ቀኑ የአፋር ህዝብ በሁለት ቤት(ገዋኔ-ሚሌ) መከከል በገዛ አገሩ እየተጋደለ በመሆኑ መከላከያ ሰላሙን ማስከበር ካልቻለ ከአከባቢው ይውጣልን የፌዴራል መንግሥት መፍትሄ ልሰጠን አልቻለም። የሚሉ መፈክሮችን ይዞ በአደባባይ መግለፁ የሚታወቅ ነው።

የመከላከያ ሠራዊት የአፋርን ህዝብን የአደባባይ ጩሀት ድምፅ ከምንም ሳይቆጥር ይህው ዛሬ በሰላም የሚኖረውን ህዝብ ለመጨፍጨፍ እና የህዝቡን ስነልቦና ለመረበሽ ፉፁም ሰላማዊ በሆኑ ገጠር አከባቢዎች በከባድ መሣሪያ እና ተሽከርካሪዎች ተግዞው ቤት ለቤት እየተንቀሳቀሱ ነው።

መከላከያ ከዚህ አስነዋሪ እና ከወታደራዊ ዲሲፕሊን ጋር የሚቃረን የአፋር ህዝብ ንቀት በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል። አንድን ግለሰብ ለህግ መቅረብ ያልቻለ ሠራዊት በአፋር ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የጥፋት ሴራ የማያቆም ከሆነ ዋ! ዋ! ዋ!

ህቡዕ_የመከላከያ_ሰራዊት_ኮማንድ_ፖሰት_በአፋር_ህዝብ_ጫንቃ_ላይ።

#ህቡዕ_የመከላከያ_ሰራዊት_ኮማንድ_ፖሰት_በአፋር_ህዝብ_ጫንቃ_ላይ።

የአፋር ክልል በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ኮማንድ ፖስት የሚተዳደር ክልል ይሁን፣ በክልሉ መንግስት የሚተዳደር ክልል ይሆን በውል ያልተለየበት ሁኔታ በክልሉ መፈጠሩ በክልሉ ህዝብ ላይ ውዥንብር ፈጥሯል።

ሰሞኑን በኢሳ ጎሳዎች በዑንዳፎዖ አከባቢ በንፁሀን የትግራይ ወንድሞቻችን ላይ የተፈጠረውን የሽብር ተግባር የአፋር ህዝብ ከዳር እስከዳር ማውገዙን ተከትሎ በስፍራው በሰላም ማስከበር ስም የሰፈሩ የመከላከያ ሀይል በጥቃት ፈፃሚዎቹ ላይ ለይምሰል እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል።
በዘመቻውም በርካታ የጦር መሳሪያዎች (23 ክላሽን ኮቭ፣40 ስናይፐሮች፣90 ሺ ጥይቶች) በኢሳ ጎሳ መኖሪያ በሆነችው #ጉሩሙድሊ መንደር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
እርምጃው ወንጀለኞችን አድኖ ለመያዝና በቀጠናው በኮንትሮባንዲስት የኢሳ ጎሳ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሚታወከውን ሰላም በዘላቂነት ለማስፍን ጉልህ ሚና የነበረው ቢሆንም፣ ጉደዩ ከገፋ ከጉደዩ ጋር በተያያዘ ረጃጅም እጆቹ እንዳሉበት የሚጠረጠረው የሶማሌ ብሄራዊ ክልል መንግስት ባለስልጣናት (የጨነቀው ነፍሰጡር ያገባል እንዲሉ)የዘመቻውን አቅጣጫ ለማሳት ግልፅ ህገ መንግስታዊ ጥሰት የተንፀባረቀበትን መግለጫ በማውጣት በአደባባይ ለሽብር ተግባሩ የነበረውን ድጋፍ ቢያሳይም፣በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃ አግኝቻለሁ በማለት ዘመቻውን የጀመረው የፌደራል መንግስትና የመከላከያ ሀይል የሽብር ተግባሩን በፈፀሙ ታጣቂዎች ላይ የጀመረውን እርምጃ ከዳር ሳያደርስ በተራና ህገ ወጥ የሶማሌ ክልል ማወናበጃ መግለጫ መቋጨቱን ለማረጋገጥ ችለናል።
ይህ በመከላከያ ሰራዊት የተጀመረው የህግ ማስከበር እርምጃን መገተት ተከትሎ በኡንዱፎኦና በገዋኒ (ኢትዮ ጅቡቲ መስመር )ላይ ( የገዋኒ ከተማዋንም ጨምሮ) ቀደም ሲል ወንጀሉን በፈፀሙ በኢሳ ጎሳ ኮንትሮባንዲስት ታጣቂዎች በአደባባይ በሚከፈቱ የደፈጣ ተኩሶች ዛሬም የንፁሃን ህይወት እንደዋዛ እየረገፈ ይገኛል።

ለዚህም ማሳያው ትናንት ከገዋኒ ወደ አምአሳቡሪ የግብርና ኮሌጅ እለታዊ ስራውን ለመከወን ወደ ሚያስተምርበት ኮሌጅ በባጃጅ ሲጓዝ በነበረ የኮሌጁ መምህር ላይ በታጣቂዎቹ አልሞ ተኳሾች የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ በቀጠናው በታጣቂዎቹ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች አነስተኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

በስፍራው ከክልሉ መንግስት ይሁንታ ይሁን፣ በጉልበትም ይሁን በውል ባልተለየበት ሁኔታ የክልሉን ፀጥታ አስከባሪዎች ከስፋራው በማስወጣት ህግን በማስከበር ስም የተሰማራው የመከላከያ ሃይል በአፍንጫው ስር በኢሳ ጎሳ በአደባባይ(በገዳማይቱ) የሚፈፀሙ የኮንትሮባንድ ንግድና በዋና አስፋልት መንገድ ላይ የሚፈፀሙ የግድያ ወንጀሎችን በመግታትና በስፍራው ህግን ከማስከበር ይልቅ ያልበላውን እያከከ ካደናገረው የክልሉ መንግስት ፈቃድና ይሁንታ ውጭ የህዝብ ቁጣን በሚቀሰቅሱ ተግባሮች ላይ በመሰማራት በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ላይ አደጋ ሊደቅን የሚችሉ አደገኛ ሂደቶችን እየሄደ ይገኛል።

ስለሆነም የአፋር ወጣቶች ይህን መርህ አልባና ግልፅ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ተደጋግሞ የሚንፀባረቅበትን የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በፅኑ ያወግዛል።
እንቅስቃሴው ለህዝባችንና ለክልላችን ብሎም በሀገሪቱ ሰላም ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደገኛ ኪሳራ በጥልቅ በመገምገም ጉዳዩ አሁንም ህግ መንግስቱን ብቻ ተከትሎ ቅድሚያ ከአድሎ የፀዳ የህግ ማስከበር ስራ ላይ እንዲቀረፅና ከጋርዮሽ የፖለቲካ ቡድኖች ጥቅም ይልቅ የዜጎችን በሰላም ወጥተው በሰላም የመግባት ህገ መንግስታዊ ዋስትና ላየደ ትኩረት ሰጥቶ የቀጠናውን ሰላም የሚያረጋግጥ ሊሆን እንደሚገባ ዱኮሂና በድጋሚ ያሳስባል።

ነቶቻችንውበታችን የሚሆኑት ስናስተናግዳቸው ብቻ ነው፤
አለበለዚያ ያወዛግቡናል ። ዩሱፍ ያሲን (አርቲክል 2012)
1. የማንነት ጥያቄዎች በየፈርጁና በየመልኩ
እገሌ የሚባል ስብስብ ለመንግሥት ምክር ቤት የማንነት ጥያቄ
አቀረበ። እገሌ የሚባለው ደግሞ በዚህ ክልል ሳይሆን በዚኛው ክልል
ልካለል አለ። ሌላው እኛ መታወቂያ መለያ አጠራሬ ይህ ነው እንጂ
ይህኛው አይደለም። አንደኛው ብሔረሰብ ልዩ ዞን (ኮንሶ) ሌለኛው
ክልል (ሲዳማ) ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አቀረበ። ስብስቦች የማንነት
ጥያቄያቸው በሕገ መንግሥት መሠረት ለመንግሥት ምክር ቤት
አቀረቡ ሲባል እንሰማለን። ይህንን ጥያቄ ያቀረቡ የቅማነት፣ የቁጫ፣
የወልቃይት፣ የዱቤ ብሔረሰብ አባላት ተገደሉ፣ ታሠሩ፣ ተቀጡ፣ ወዘተ
ሲባል እንሰማለን። ገሚሱ የማነት ጥያቄ ቀላል መልስ አለው።
ገሚሱ ቀላል መልስ የለውም።
ማንነትን ማጠንጠኛ ያደረጉ ጥያቄዎች መልስና መፍትሔ
የሚጠበቀው አንዳንዴ ጊዜ ከመንግሥት አካል (የመንግሥት ምክር
ቤት፣ ክልል) ነው። በሌላ ጊዜ በባለጉዳዩ ስብስብ እንዲወሰን
ይፈለጋል፣ ይደረጋልም። አንዳንድ ጊዜ ችግሩ ማኅበራዊ በስብስቦች
መካከል ነው። ሌላ ጊዜ በመንግሥት አካልና ስብስቦች መሃል ነው።
የዛሬ 8 ወር ጀምሮ በኦሮሞ ክልል፣ ሰሞኑን ደግሞ በጎንደር
መሳሳቦች መንስኤቸው ማንነት ነው ተብሏል። ማንነት በሀገሪቷ ባሉት
ባለድርሻ ስብስቦች ቀጣይ አብሮነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ
ሕልውናዋም ጭምር ከሁሉም ችግሮች በላይ ተፈታታኙ በታኝ
ተግዳሮት የጋረጠ ጉዳይ የሆነ ነው። ይህም ከቀርብ ጊዜው ወዲህ
እኛ ብቻ ሳንሆነ የገዢው ፓርቲ ወገን የነበሩ የቀድሞ ጀኔራሎችም
ጭምር እያሳሳባቸው መጥቷል። ሁሉም የማንነት ነክ ጥያቄዎች
ተመሳሳይ ይዘትም ሆነ ቅርጽ የላቸውም። በመዛኙ በማንነት ዙርያና
ሳቢያ የተነሱ ጥያቄዎችና ያስከተሉ ውዝግብ ዥንጉርጉር ቢሆንም
ቅሉ አብዛኛዎቹ ያነታርካሉ። አልፎ ተርፎ ያወዛግባሉ። አንዳንድ ጊዜም
ጦር ያማዝዛሉ። ለምን?
2. ዛሬም ማንነትን ማጠንጠኛ ያደረጉ ጥያቄዎች ለምን ያነታርኩናል?
የዛሬ ስንት ዓመት ያውም መልስ ያላገኘ የማንነት ጥያቄ የለም
ከተባለ ጊዜ በኋላ። 50 ዓመት ዋልልኝ መኮነን የተባለ የፖለቲካል
ሳይንስ ተማሪ ሰመ ጥሪው አርቲክል ከጻፈ በኋላ። 23 ዓመት ሀገሪቱ
ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጥያቄ መልስ የሰጠ ሕገ መንግሥት ከተረቀቀ
በኋላ። ታዲያ ስብስቦች ለምን ይወዛገባሉ? ስብስቦች እርስ በርስ
ይጋጫሉ፣ ከመንግሥት ጋር ያጋጫሉ። ድሮ አፋርና ኢሣ በውኃና
ግጦሽ ይጋጫሉ ይባል ነበር። ያሁኑ ጥያቄዎች የመሬት ይገበኛል
ጥያቄዎች ብቻ አይደሉም። የሥልጣን፣ የሃብትና የተጽእኖ ማሳረፍ
ዙሪያ የሚደረጉ ናቸው። ያሁኑ ጥያቄዎች የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎች
ብቻ አይደሉም። ዛሬም ማንነትን ማጠንጠኛ ያደረጉ ጥያቄዎች ለምን
ያነታርኩናል? ጥያቄን ከመመለሳችን በፊት በቅድሚያ ማንነት
ምንድነው የሚትለዋን ጥያቄ ባጭሩ ለመቃኘት ቢንሞክርስ!
3. ለመሆኑ፣ ማንነት ምንድነው?
በቀላሉ አማርኛ በልዩነት ላይ የተመሠረተ ወገንተኛነት መገለጫ
ነው። መለያ ነው፣ ካንድ ስብስብ አባለት ጋር የምገለጸው ልዩነት፣
ከሌላው ስብስብ አባለት ጋር አለን የሚንለው አንድነትና ወገንተኛነት
መሠረት ያደረገ ወገንተኛነት ነው። ማንነት፣ ባጭሩ አንድ ስብስብ
እሱን ከሌሎቹ ስብስቦች የሚለዩትን መታዋቂያ መለያዎቼ ናቸው
በሚላቸው ተጋሪዮሾች (COMMONNESS) ላይ ተሞርኩዞ
ወገንተኛነት የመፍጠር ክንዋኔ ነው። ሥልጤ ፣ ሥልጤ እንጂ ፣ ጉራጌ
አይደለም። ወልቃይት ጠገዴ አማራ እንጂ ትግራዊ አይደለም። የለም
ወልቃይት ትግራዊ ስለሆነ በትግራይ ክልል ውስጥ መካለል አለበት።
ቁጫ፣ ቁጫ እንጂ ጋሙም፣ ጎፋም፣ ወላይታም አይደለም። ኦሮሞ
ሀገሩ ኦሮሚያ እንጂ፣ ኢትዮጵያ አይደለም። ማንነት (identity)
በቀላሉ አማርኛ የመለያ መታወቂያ ሊባል ይችላል። “እነሱ” እና “እኛ”
ተባብለው “እኛን” “ከእነሱ” በሚለያቸው ተጋርዮሾች መግለጫዎች
ፈልገውና ላንዱ ወገን ወገንተኛት መፍጠር ነው። በሌላ በኩል “
የሌላኛውን” (The other) ዝምድና መካድ ብቻ ሳይሆን ከእሱ ጋር
መፋጠጥ ነው። ገሚሱ ማንነቴ ይታወቅ (እውቂያ ይሰጠው?) ነው
ጥያቄው፣ ገሚሱ ደግሞ በዚህ እውቂያ መሠረት ራሴን በራሴ
የማስተዳድርበት የራሴ ወረዳ፣ ዞን፣ ክልል ይሰጠኝ ይላል። ሌላው
በኢትዮጵያ ውስጥ ባንድነት እንኑር ወይስ ለእየብቻቻን የራሴ ጎጆ
እንቀልስ ባዮች ደግሞ አሉ። ሌላው በተለያዩ ምክንያቶች አብረን
መኖር ስለማንችል የራሳችን መንግሥት እንመሥረት ብሎ ይነሳል፣
ይቀሰቅሳል። ይህ ስሜት ወደ ኢዶሎጂ ብሎም ወደ እንቅስቃሴ
ያድጋል። ባንድ ላይ ብሔረተኛነት የሚሰኘው ይህው ስሜት፣
ኢድዮሎጂና እንቅስቃሴ ቢባል ያስኬዳል እንደዚህ ናቸው ማለት
ይቻላል። እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች ስብስቦችን
ያነታርካሉ፣ ያነታርኩናል፣ ያወዛግቡናል። አልፎ ተርፎ አቧድነው፣ ጎራ
አስለይተው፣ ጦር ያማዝዙናል። ዛሬ በጎንደር የምንመለከተው
አተረማማሽ ሆኔታ መንስኤቸው ማንነትና ማንነትን ማጠንጠኛ ያደረጉ
ጥያቄዎች ናቸው።
የሰው ልጅ ስብስቦች እንጋራለን የሚሉትን የማንነት መገለጫዎች
መሠረት አድርገው የሚፈጥሩት የወገንተኛነት መገለጫዎች በርካታ
ናቸው። እዚህ ለመዘርዘር ያስቸግራል። ሁሉ ግን ባንድ ሚዛን
የሚመዘኑም አይደሉም። ሚዛን የሚደፉ አሉ። ሚዛን የማደይፉ
ተጋሪዮሾች ይኖራሉ። የሰው ልጆች ስብስቦችን መቧደን መነሻ
በማድረግ በመካከላቸው የሚፈጠረው አለመግባባት ፈረጀ ብዙ።
በተለያዩ ርእስ ግዳዮች ይጋጫሉ። አንዳንዱ ተጋሪዮሾቹ ከሌሎቹ
ይበልጥ ወሳኝ ናቸው። ይበልጥኑም ያወዛግባሉ። የዘር ወይም ያንድ
ቋንቋ ስብስብ ወይም ያንድ እምነት ወገንተኛት ላይ የተመሰረተው
“እኛ” እና “እነሱ” ተሰናኝተው መቧደን ነው እንግዲህ የዓለማችንን
ህዝቦች የሚያነታርከው ፤የሚራኩተውና አልፎ ተርፎ ጦር እያማዘዘ
የሚያገዳድለው። ገና ዓላማችን ያወዛግባሉ የተባሉትም እነዚሁ ሁለቱ
አናቋሪ የማንነት መግለጫዎች ናቸው።
4 መቧደንና ውዝግብ
• ማንነት በልዩነቶቻን ላይ የተመሠረት ወገንነተኛነት ነው እስከተባለ
ድረስ፣ ልዩነቶቻችን ማስተናገድና ማስተዳደር እስካልቻልን ድረስ
ያወዛግቡናል። ይህ ውዝግብ ነው ለቁሩቁሱ ምክንያት። ሰለዚህ
ማህበራዊ ስብስቦች በቡደን ቡደን መቧደናቸው አይደለም ወደ
ግጭት የሚያመራቸው ተፃራሪ ወይም በጊዜው ተፃራሪ
የሚመስላቸው ግቦችን በየፊናቸው ለመምታት ወይም ለማሳካት
ማለማቸው እንጂ። ይህ ድርጊት ነው እንግዲህ ውዝግብ
የሚሰኘው። የውዝግብ (Conflict) አጥኚዎች፣ ውዝግብ ”ሁለት
ወይም ከዚያ በለይ የሆኑት ወገኖች ተፃራሪ ሆነው የሚታያቸውን
ዓላማዎች አንግበው አንዱ የሌላው ዓላማ ግብ መምታት
እንዳይይሳካ የማድረግ ክንዋኔ ነው” ይሉናል። በግለሰቦች መካከል
በነጠላ ማንነታቸው የሚነሱትን አለመግባባቶች ለጊዜው ከዚህ
ውጭ እናድርጋቸውና ሌላውን እንመልከት። ሰዎች ሕወታቸውን
ሲመሩ የተለያዩ ግቦች አንገበው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል። በዚያኑ
መጠን ተፃራሪ የሚመስሉ ፍላጎት ፤ ዓላማ ፤ ጥቅምና አመለካከቶችን
ያራምዳሉ። እነዚሁ ሌሎቹ ካነገቡትና ከሚያራምዱት ሳይጣጣሙና
የተቃረኑ ሲመስሏቸው ይሻኮታሉ፤ይሯኮታሉ፤ይቆራቆሳሉ። ባጭሩ ጠብ
ይፈጥራሉ። ባንድ ዓላማና ፍላጎት ተፃርረው ጎራ ላይተው ሁለቱም
የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካትና በዚያኑ መጠን የሌለኛውን ዓለማ
ስኬት ለማደናቀፍ አልፎ ተርፎ ወድቅ ለማድረግ በየፊናቸው
ይፍጨረጨራሉ። በዚያኑ ወቅት ዓላማዎቹ ተፃራሪ ሰለሆኑ ወይም
ለግቡ አንጋቢዎች ተፃራሪ ዓላማዎቻቸን ማጣጣም የማይ

ቻል ሆነው
ሰለሚታዩዋቸው የግድ ጎራ ይለያሉ። ይፋጠጣሉ። ደረጃው ይለያያል
እንጂ ለውዝግብ ተመራማሪዎቹ ከቤተሰብ አለመግባባት እስከ
ሶማሊያው ዓይነቱ አመሰቃቃይ እርስ በእርስ ጦርነት የመሳሰሉት
ቁሩቁሶች ሁላ በውዝግብ ውስጥ ነው የሚጠቃለሉት። ሰለዚህ
በቡድን ቡድን መቧደኑ አይደለም ወደ ግጭት የሚያመራቸው ተፃራሪ
ወይም ተፃራሪ የሚመስላቸው ግቦችን ለመምታት ማለማቸው እንጂ።
በመካከላቸው “ውዝግብ” ተፈጠረ የምንለው ይህው አለመግባባትና
አለመጣጣም ሲከር ነው።
• የማንነት ፖለቲካ መሠረቱ እነዚህን ልዩነቶቻችንን መሠረት አድርጎ
ወገን ለይቶ መደራጀትና አንዱ ከእነሱ የተለየውንና “ሌላው”
ከተሰኘው ጋር ተፃርሮ መፋጠጥ ነው። አንዳንድ ጊዜም በጦር ሜዳ
መግጠም ነው። ያን ጊዜ ልዩነቶቻችን ጌጦቶቻችን ሳይሆኑ የጠብ
መነሾ ሆነው ቁጭ ይሉና ያነታርኩናል፣ ያወዛግቡናል። አልፎ ተርፎም
አቧድነው፣ ጎራ አስለይተው፣ ጦር ያማዝዙናል።
• ልዩነቶቻችን ጌጦቻችን ናቸው ከሚለው መፈክር አሸጋግረን
ልዩነቶቻችንን ማስተናገድና ማስተዳደር አልቻልንበትም፣ በረዥሙ
ታሪካችን። እስካሁን አላወቅንበትም ማለት ሳይሻል አይቀርም። እነሱን
ከማስተናገድና ማኔጅ ከማድረግ ይልቅ ልዩነቶቻችን ከእነጭራሹ
መካዱ ይቀናናል። እኛ አንድ ነን፤ የምን ልዩነት አመጣችሁብን ደግሞ
ማለቱን የምናዘወትርም አልጣፋንም። በእኛ መካከል ልዩነት
የሚፈጥሩት የውጭ ጠላቶቻችን ናቸው በማለት በሌላው ላይ
ማላከኩን የምንመርጥበት ጊዜም አለ ። ጉራማይሌነታችን
ከእነአካቴው ሽምጥጥ አድርጎ መካድም ብቻ ሳይሆን በጉልበት
እንዲወገዱ መጣሩ ሌለኛው አደገኛ አካሄድ ነው። በርካታ አብነቶችን
መጠቀስ ይቻላል። ከረዥሙ ታሪክችን በግድ አንድ የማድረግ
ሙከራዎች ውስጥ ሁለት አብነቶች ብቻ እንመልከት። በመንግሥታዊ
ሥልጣን የተደረጉ እምነትን በጉልበት አንድ የማድረግ ሙከራዎች።
መላው የሀገሪቷ ህዝብ በኃይማኖት አንድ ማድረጉ በኢማም አሕመድ
ግራኝ በ1529/1543 ተሞክሮዋል። የዛሬ 480 ገደማ። ብዙ ጥፋት
አደረሰ እንጂ የሀገሪቷን ህዝብ ማስለም ወይም በግድ ሙስሊም
እንዲሆን የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። በ1877 በቦሩ ሜዳ አፄ
ዮሃንስ ሙስሊሞችን በሙሉ ክርስቲያን ሁኑ ወይም “ክስትኑ” ብለው
በንጉሣዊ አዋጅ ለማጥመቅ የተደረገው ሙካራም እንዲሁ
አልተሳካም። ዛሬ በግድ አንድ እንድርግ ብሎ የሚነሳ ወገን ባይኖርም
ማስተናገድ ተሳክቶልናል ማለትም በፍጹም አይቻልም።
ባንድ መንግሥት ሥር ለመተዳደር ከወሰኑ በኋላም ቢሆን
መንግሥቱን በምን መልክ እናደራጅ ጥያቄ ብሔረሰቦችን ያነጋግራል።
ባንድ ሀገር አብርን ለመኖር ብንወሰን አሁንም የወደፊቱ አብሮነታችን
በምን መልኩ ይደረጅ በሚለው ሃሳብ ላይም የሁሉም ስምምነት
ያስፈልጋል ። የተወሰነው ክፍል የራሴ እድል በራሴ ልወስን ካለ
አስቸጋሪ ሆኔታ ይፈጠራል። ያለፉ የታሪክ ስህተቶቻችን የወደፊቱ
አብሮነታችን አይታሰቤ አድርጎታል ከተባለም ለዚህ ችግር መፍትሔ
እንደሚያስፈልግ ከሀገራችን ተሞክሮ መገነዘብ አይገድም። አስቸጋሪ
ነው አልኩኝ እንጂ መፍትሔ የለውም ማለቴ አይደለም። ጉዳዩ
አስቸጋሪና የተወሳሰበ የሚሆነው ግን አንዳንድ ስብስቦች በአብሮነት
መኖሩን አሻፈረን ብለው የራስ መንግሥት መመሥረት አመለካከትና
እቅድ መንደፍ ሲጀመሩ ብሔረተኛነት ሥር እየሰደደ መጣ እንላለን።
ለመሆኑ ብሔረተኛነት ምንድነው?
5. ለመሆኑ ብሔረተኛነት ምንድነው?
አንድ ስብስብ የራሴ ናቸው የሚላቸውን አባላት ባንድ መንግሥት
አሃድ ወይም ትድድር ሥር እንዲጠቃለሉት ምኞቱን ተግባራዊ
ለማድረግ የሚያደረገው እንቅስቃሴ መግላጫ ተደረጎ እስከ ተወሰደ
ድረስ ከፖለቲካዊ ክውን ወይም አሃድ ውጭ ከቶ ሊታሰብ
አይችልም። ብሔርተኛነት ከመንግሥት ውጭ ሊታይ አይችልም።
በዚህ ጽሑፍ በዚህ አግባብ ነው እየተጠቀምኩበት ያለሁት።
ከመንግሥት ወይም ከብሔር ማዕቀፍ ውጭ ብሔርተኛትን ማሰቡ
አስቸጋሪ የሚያደረገው ይህ ይመስልኛል። በሌላ በኩል፣ በማንነቱ
ወገንተኛት የተደራጀ ኃይል ሁሉ የራሱን መንግሥት ወደ መመሥረቱ
አያመራም። ከላይ በሥልጤ ብሔረሰብ ምሳሌነት የተመለከትነው
ወገንተኛነት ዓላማውና ግቡ ሥልጤን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ የራሱን
መንግሥት ወይም ፖለቲካዊ አሃድ የመስረት ግብና ዓላማ
አልነበረውም። የለውምም። የተወሰኑ ብሔረሰቦች ከራሳቸው ጋር
ለተያያዙ የአስተዳደር ጥያቄዎችና ችግሮች እልባት እንዲያገኙላቸው
መፈለጋቸው እንደተጠበቀ ሆኖ። ብሔርተኝነት እንደ ማንነት ማደራጃ፤
ብሔርተኛነት እንደ ስሜት ፤ብሔርተኛነት እንደ እንቅስቃሴና
ብሔርተኛት እንደ ኢድዮሎጂ በብዙ ትርጉም፤ፊቺና ደርዝ ያለው
ማስገንዘቢያ ንባበ ቃል ነው። ወደዚያ ዝርዝር እዚህ ላይ አንገባም።
6. የአብሮነት መፍትሔ ፍለጋ
• ማንነት በልዩነት ላይ የተመሠረተ ወገንተኛነት ነው ከተባለ፣
ልዩነቶቻችን ማስተናገድ ካልቻን ያለጥርጥር ያወዛግቡናል። የግድ
የአብሮነታችን መሠረት በመሆኑ የመንግሥት አደረጃጀት አማኻኝነት
አኗኗሪ ቀመር እንሻለን የምንለው ለዚህ ነው። ያልተማከለ ፌዴራላዊ
ሥርዓትም የተመረጠውም ለዚሁ ነው። ከላይ የተመለከትናቸው
በማንነት ዙሪያ ያጠነጠኑ ጥያቄዎች መልስ ማገኘት ይኖርባቸዋል፣
ከማንነት እውቂያ ጀምሮ፣ አከላለል፣ ራሳቸው በራሳቸው
የሚያስተዳድሩበት አሃድ ደረጃ፣ በራሳቸው ጉዳዮች ላይ የመወሰን
ሥልጣንና ተግባራዊነቱን ይመለከተል። በተለይም ባልተማከለ
የመንግሥት አወቃቀር። የተዘረጋው ፌዴራላዊ ስርአት በተለያዩ
ምክንያቶች የተተለመለትን ግብ ማሳካት አልቻለም።
• የተወሰኑትን ለመጠቃቀስ፣
o የገዢው ፓርቲና መንግሥት የማንነት ጥያቄን እንድ አንደ
ማተረማመሻና የሥልጣን እድሜ ማራዘሚያ አድርጎ
መጠቀሙ፣
o በዚህና በሌሎች ተዛማጅ ምክንያቶች ፌዴራልዊ ሥርዓትን
በቅጡ ተግባራዊ ማድረግ አለመቻል፣
o የአከላለል ችግሮች
o የመልካም አስተዳደር ችግሮች
• እነዚህን ችግሮች መፍታት በራሱ በቂ ሊሆን አይችልም። ባጭሩ፣
ለነዚህ ያልተማከለ ፈዴራላዊ አወቃቀርን ለተበተቡ ችግሮች መፍትሔ
መፈለጉ ነው የሚያዋጣው። እንደገና ወደ ተማከለ አሠራር አስወግዶ
ከማዕከል ለመተዳደር ተቀባይነት በብዙዎቹ ዘንድ በግምት መግባት
አለበት ። ስለዚህ ኢማዕከላዊነት ወይም ያልተማከለ አውቃቀር እንጂ
ወደ አሃዳዊ አሰራር መመለሱ ከምንፈታው ችግር ይልቅ
የሚያወሳሰባቸው ችግሮች ያሳስባሉ።
እነዚህን ልዩነቶች ማስተናገድ ነው በተለይም በመንግሥት
መንግሥታዊ አወቃቀር አማካኝነት አኗኗሪ መፍትሔና ፎርሙላ
መፈለጉ የግድ ነው ። በአጠቃልይ ሁሉም ራሱን የሚመለከቱ
ጉዳዮችን በራሱና በዚያው በአካባቢው በራሱ በተመረጡ ወኪሎች
እንዲወሰኑለት ፍላጎት ይስተወላል። ይህ ደግሞ ያልተማከለ አሰራር
ነው። ኢማዕከላዊነት ወይም ያልተማከለ አወቃቀር አንዱ ቅርጽ
ደግሞ ፌዴሬሸን ነው። በዓለም ከ25 ሀገራት በላይ ፌዴራላዊ
አደረጃጀት አላቸው። በህዝብ ብዛት ሲሰላ ግን ከዓለማችን ህዝብ
አብዛኛው ክፍል የያዙ ናቸው። በሀገራችን ላለፉት 24 ዓመታት
የተሞከረው ፌዴራል ሥርዓት ዝርጋታ ግን ካላይ ከተመለከትነው
ጉድለቶች በተጨማሪ በበርካታ የአከላለል መፋለሶች የተተበተበ ሆኖ
ተገኝቷል። ስለዚህ ፌዴራል ሥርዓቱን ማወጅ በራሱ በቂ አይደልም።
7. ከማነቶች መራኮት እስከ አኗኗሪ ቀመር አብሮ መንደፍ
“ልዩነቶቻችን ውበቶቻችን ናቸው” የተሰኘው ውብ መፈክር ተግባራዊ
ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲን በቅጡ ለመማማር በቅድሚያ
ልዩነቶችን መቀበል ይኖርብናል። “ሌላኛው መቀበል” የዲሞክራሲ
“ሀ፣ ሁ” ነው ይላሉ ጠበብቶቹ። ምክንያቱም የሌላውን ግለሰብ
ወይም ስብስብ ፖለቲካዊና ኃይማኖታዊ አመለካከት

መቀበል አብሮ
መኖር የግድ የሚለው ግዴታችን ነው ለማለት ያስደፍራል። በሌላ
በኩል፣ ሌላኛው አለመቀበልና አመለካከቶችን ማስተናገድ አለመቻል
ራሱ ልዩነቶች ካለመቀበል ጋር በቅርብ የተቆራኘ አካሄድና አመለካከት
ነው። ከታሪክም ከዛሬው ተጨባጭ እውነታ። እንዲያውም አብዛኛው
ችግሮቻችንም የሚመነጩት ከዚህ ጉድለት ነው ማለቱ የቀላል።
ዲሞክራሲ በመሠረቱ ከእኛ የተለየውን “የሌለኛውን” አመለካከት
መቀበል ወይም ማስተናገድ የመቻል አካሄድና አግባብ ነው እስከ
ተባለ ድረስ። የራስን ጉዳዩ በየደረጃው በራስ በተመረጡ አካላትና
ግለሰቦች ማከናወንንም ይጨምራል። የዲሞክራሲያዊ አግባብነቱ
መሠረትም ይህ ምርጫና ተጠያቂነት ነው።
8. ማጠቃለያ
በቅድሚያ ልዩነቶቻችንን አስተናግደን ማስተዳደር ስንችል ብቻ ነው
ለዜግነታዊ መንግሥት መሰረት የምንጥለው። እሱም ተግባራዊ
የሚሆነው ገባር ወይም ቅርንጫፍ ማንነቶችን በአስባሳቢ ማንነት
ማቀናጀት ስንችል ነው። የዜግነት መብት ማዕከል ያደረገ አሰባሳቢ
ማንነት ብቻ ነው እነዚያ የተመለክትናቸው አነታራኪ የሆኑትን
የቅርንጫፍ ማንነቶቻችንም ሁላ አዋህዶ ልያስተሳስረን ብቃት ያለው።
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር፣ የኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ ባንድነት
የሚያኗኑረን ቀመር ካለም እሱ ነው። እጣ ፋንታችንም እሱ ነው።
ባጭሩ ተቻችሎ መኖር መሠረቱ ፤ማገሩና ግርግዳው እሱ ነው።
ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ የምንመለከታቸው የብሔረሰብና
የኃይማኖት አለመግባባቶች የገዢው ፓርቲ የራሱን የሥልጣን እድሜ
ማራዘሚያ አድርጎ የተከተላቸውን ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው መባሉ
የተወሰነ እውነተኛነት ያለው አባል ነው። በከፊል ገዢው ፓርቲ
የተከተለው አግላይ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው። በሥልጣን ያለው
መንግሥት ሆን ብሎ ልዩነቶቻችን እንዲሰፉ ሲያደርግ ተመልከተናል።
የሚያለያዩን ጉዳዮች እንጂ የሚያስተሳስሩን ችላ ሲባሉ አይተናል።
ማንነት በመሠረቱ ልዩነት ነው ካልን ይህ ልዩነት የሚገለጽባትውን
ፖለቲካዊና አመለካከታዊ አብዛሕነት (DIVERSITY) መቀበልና
ማክበር ነው ቀዳሚው። ስለዚህ በልዩነት ላይ የተመሠረተ
ወገንተኛነት መኖሩን እስተቀበልን ድረስ መፍትሔው ይህንን ልዩነት
መቀበልና ማስተናገድ ነው። በተለይ በመንግሥት መዋቅር ላይ ያለን
ግንኙነት ማስተዳደር መቻል ነው። ስለዚህ “It is NOT our
differences that divide us. It is our INABILITY to
recognize, accept and celebrate those DIFFERENCES”
የምትለው አባባል የተለየ ትኩረትን የምትሻ ናት። ከሁሉም በላይ
እነዚህት ልዩነቶች ማስተናገድና ማስተዳደር ሊኖርብን ነው፣
በተለይም በመንግሥት አደረጃጀትና በምንዘረጋው አኗኗሪ ፎርሙላ
አማኻኝነት። መሠረቱ በየደረጃው ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት
የአብላጫው ይሁንታ በምርጫ የታከለበት ዲሞክራሲያዊ አግባብት
ነው። የማንነት እውቂያ የሚያቀርቡ ስብስቦች ፣ እውቂያን ከተቀዳጁ
በኋላ በደረጃዎ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት አሃድ
(ክልል፣ ዞን፣ ልዩ ወረዳ … ወዘተ) ይጠይቃሉ። ለነዚህ መልስ
መስጠቱ ለብቻው ግን በቂ አይደለም።
እነዚያ ከላይ የተመለክትናቸው አነታራኪ የሆኑ ቅርንጫፍ ማንነቶችን
ሁሉ አዋህዶ ሊያስተሳስረን ብቃት ያለው የዜግነትን መብት ማዕከል
ያደረገ አሰባሳቢ ማንነት ነው። የሚያለያይ ሳይሆን የሚያስተሳስርና
የሚያሰባሰብ እንሻለን ማንም ይግዛ ማንም ገዢው የዜጋውን መብት
ሊጥስ የማይችልበት ሕጋዊና ተቋማዊ ዋስትናዎች የሚያረጋግጥ
አዲስ መንግሥት፣ በአዲስ መሠረቶች መገንባቱ ነው ቅድሚያችን
መሆን ያለበት። ዜግነታዊ መንግሥት የምንለው እነዚህ ሁሉ አጣምሮ
የያዘ አግባብና ሥርዓት ነው በማለት ንግግሬን እዚሁ ልቋጭ።
ከላይ የውይይት መንደርደሪያ ማጠንጠኛ ያደርግኳቸው ማንነት፤
ውዝግብ፤ ብሔረተኛነትና የመሳሰሉ ፅነሰ ሃሳቦችና ማስገንዘቢያ ንባበ
ቃሎች ባለ ብዙ ፊቺ፤ትርጉምና ፈረጅ እንደ ሆኑ አልሳትኩም። በአጭር
ደቂቃዎች ንግግር እነዚህ ጽንሰ ሃሳቦች ተዛምዶ፤ ተያያዥነትና
መወሳሰብ በሚገባ አብራራለሁ የሚል የተሳሳተ ግምት የለኝም።
በጥያቄና ውይይት ጊዜ ልንዳብራቸው እንሞክር!!
አመሰግናለሁ!!
ማስታወሻ፡- ይህ ጽሑፍ የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፤
“ፌዴራሊዝም እና የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ሐምሌ
22 ቀን 2008 ዓ.ም. ደን ሐግ በተሰኘችው የኔዘርላንድ ከተማ
ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ በአቶ ዩሱፍ ያሲን ለውይይት የቀረበ ነው።

Afar information centers

የመሪነት ቀውስ (Lየመሪነት ቀውስ (Leadership Crisis)
የአመራር ቀውስ እሚፈጠረው በመሪዎች ተፈጥሯዊ ባህሪና ፣ ወቅቱ በሚፈጥራቸው ችግሮች የተነሳ ነው ። ሌላው ደግሞ በመሪው መሀከልና በተከታዮቹ ወይም በሚመራው ህዝብ መሀከል መረዳዳት በማይኖርበት ጊዜ አለመግባባትና የተከታዮች ተቃውሞ እሚከተለው ። መሪዎች የህዝባቸውን ፍላጎት ወይም ላይረዱ የሚችሉበት ምክንያት ካለማወቅ ወይንም ፣ ከራስ ፍላጎት አንፃር ብቻ ከማየት ፣ ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን የመሪነትን ቀውስ ከሚያስከትሉ ነገሮች ዋነኛው ተደርጎ ሊወስድ የሚችለው ይኀው ጉዳይ ነው ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ እንዳለ አንድን ችግር መጀመሪያ ላይ ሲፈጠር መለየት ቢያስቸግርም ችግሩ ከታወቀ ግን መፍትሄው ቀላል ነው ። ይሁን እንጂ ውሎ አድሮ ግን አንድ ችግር ሲነሳ ካልታወቀ ውሎ አድሮ ችግሩ ቢደረስበትም መፍትሄው ግን የራቀ ነው ፣ ለመፍትሄ በዘገየበት ሰአት ነው ። በዚህ ወቅት ሁሉም ሰው ችግሩን ቢረዳውም መፍትሄውን ለማግኘት ግን ዘግይቷል ። ስለዚህ ሲጀመር ችግሮችን የመለየትና የማወቅ ለአንድ መሪ የኋላ ዘመን ስኬት ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው ።
ቀውስን በተመለከተ የተለያዩ አመለካከቶች አሉ ። አንዳንድ ጊዜ የመሪነት ቀውስ መከሰት ችግሮች ፈጠው እንዲወጡና መፍትሄን እንዲያገኙ ያደርጋል ብለው አንዳንድ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፤ በሀገርኛው አባባል ካልደፈረሰ አይጠራም እንደማለት ሲሆን ፤ ኔቼም ቀውስ ሲፈጠር ነገሮች ፈጠው ይወጡና ችግሮች መፍትሄን ያገኛሉ ተብሎ ይታመናል ። ነገር ግን ይሄ ሊሆን የሚችለው መሪው መፍትሄን መስጠት ካልቻለ ለሚመራው ተቋም እንደ አማራጭ ሊሆን ይችላል ። ይህም ቢሆንም ግን መሪው የሚሞገሰው ቀውስን መፍታት በመቻሉ ነው እንጂ በቀውሱ ተሸንፎ ከአቅሙ በላይ ሆኖ ነገሮች ሲለይላቸውና ሲፈነዱ አይደለም ፣ እንደው ማንም ሰው በሚረዳው ሁኔታ ከአቅሙ በላይ የሆነ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ።
ሌላው የመሪዎችን የመምራት ብቃትን የሚቀንስ ነገር መገለል(Isolation)ነው ። መሪነት ማለት በሰዎች መሀከል ማህበራዊ እንቅስቃሴ ባለበት ውስጥ የሚሰራ ነገር ነው ፣ እንጂ እንደ ሳይንቲስቶች በላብራቶሪ ውስጥ ለብቻቸው ሆነው እንደሚያደርጉት ምርምር የሚከናወን ነገር አይደለም ።መሪዎች በመገለል ውስጥ ካሉ ስራቸውን መስራት አይችሉም- መገለል የመሪውን የመምራት ብቃትም ሆነ አካባቢውን የመረዳትና የመቆጣጠር በንቃቱን በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርገዋል ። መሪዎች ራሳቸውን ያገለሉ ከሆነ ወይንም ከሌሎች ጋር የማይቀላቀሉ ከሆነ ፈላጊያቸው እየቀነሰና በዙሪያቸው እየሆነ ያለውን ነገር የመቆጣጠርና የመረዳት ችሎታቸውን ያዳክማል ፤ በማንኛውም መንገድ መሪዎች ይህን መከላከልና የሚደረገውን ነገር ከስር ከስሩ ማየትና መረዳት መከታተልና አስፈላጊውን ማስተካከያ እያደረጉ መቀጠል አለባቸው ። መሪዎች ስራዎቻቸውን እሚያደናቅፉባቸውን በማጋለጥ እንዲገለሉና ፣ ከመንገዳቸው ገለል እንዲሉላቸው የሚያደርጉበት ስልትም እንደመሆኑ ፣ እነሱም በሌሎች ሆነ ተብሎ የመገለል ወጥመድ ውስጥ እንዳይገቡ ራሳቸውን ነቅተው የሚጠብቁበት ስልት ነው ።
ውድድር ያለበት ወይም ውድድር እንዲኖርበት በሚፈለግ ሁኔታ ፣ አንድ መሪ ውድድሩን ካጠፋ ፣ የራሱን የሚመራውን ተቋም እድገት ያቀጭጨዋል ። ለተቋሙ ወይም ለሀገሪቱ የፖለቲካ እድገት እገዛን ሊያደርግ ይችል የነበረውን ፣ እንዲሁም ለወደፊቱ ሽግግር ወቅት ሲመጣ ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖር የሚያስችለውን ተቋማዊና ፣ እውቀትና የሰው ሀይል እድገት እንዲጫጭ ነው እሚያደርገው ። የጤናማ ውድድር መኖር ለተቋማትም ሆነ ለመንግስታት እድገትና ጥንካሬ አስፈላጊ ነው ። ለምሳሌ መሪው የሚመራው የንግድ ድርጅት ቢሆን እንኳን ተወዳዳሪ ድርጅቶችን በሙሉ ከገበያ ቢያስወጣና ብቻውን ገበያውን ቢቆጣጠር ራሱን በራሱ መልሶ መብላትና ፣ ብቸኛ የገበያው አቅራቢ ወይም ሻጭ መሆን ሲሆን ይህም በማህበረሰብ ደረጃ ሲታይ ከሚያስገኘው ትርፍ ይልቅ የሚያመጣው ጉዳት ሲያይል ነው ።
ያም ብቻ ሳይሆን በታሪክ በርካታ ግዙፍ በብቸኝነት ገበያውን የተቆጣጠሩ ሞኖፖሊዎች የተፈጠሩ ሲሆን ሞኖፖሊዎች ውድድር ስለሌለ ራሳቸውን በራሳቸው ወደ ማጥፋት እንደሚያመሩ ሲረጋገጥ ሞኖፖሊ የነበሩ ኩባንያዎችም በጊዜ ሂደት ህልውናቸውን እያጡ ወይም እየተዳከሙ በመሄድ በሌሎች በአዳዲስ ተተክዋል ሄደዋል ። ሞኖፖሊዎች ሌላም አደጋ አለባቸው ይኀውም የገበያው ሁኔታ በራሱ የሚቀየርበትና ሞኖፖሊ ኩባንያዎች ሳያስቡት የገበያ ድርሻቸው በሌሎች የሚወሰድበትና መወዳደር የሚያቅታቸው ሁኔታም ሊፈጠር ይችላል ።
አንድ መታወቅ ያለበት ለአንድ ሀገር ፖለቲካው ከምጣኔ – ሀብቱ እድገት በላይ ሲሆን ፣ ልዩነቶችን እሚያስተናግድ የፖለቲካ ስርአት ከጊዜያዊ የምጣኔ – ሀብት እድገት በረጅም ጊዜ ለአንድ ሀገር የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል ። ይህ ብቻ ሳይሆን ልዩነችን ማስተናገድና የተለዩ ሀሳቦች እሚገለፁበት መንገድና እድል መኖር ከማፈን ልዩነቶችን ማስተናገድና የተለያዩ ሀሳቦች እሚገለፁበት መንገድና እድል መኖር ከማፈን ይልቅ የተሻለ ነው ።
በመሪነት ውስጥ በጣም የሚፈራው ጉዳይ የስርአት አልበኝነት (Anarcy) መፈጠር ነው ። ሌላው ደግሞ መሪው ለምሳሌ ተቃውሞ ቢነሳበት ወይንም ስርአት አልበኝነት ቢፈጠርበት ሀይልን በመጠቀም የተወሰኑ ሰዎችን መስዋእት (Scape goat) በማድረግ ያንን ተቃውሞ ለጊዜው ሊገታ ይችላል ፤ ነገር ግን ዋናው የነገሩ መነሻ ጉዳይን አውቆ ካላከመ በስተቀረ ከበሽታው ይልቅ ምልክቱን ማከም ይሆንበታል ፤ ነገር ግን ነገሩን ከስሩ ከፈታው ያ ችግር ዳግም ተመልሶ እንዳይመጣ ሊያደርግ ሲችል ፣ ምልክቱን ብቻ ማለትም ስርአት አልበኝነቱን ብቻ ሊያስቆም ቢችል እንኳን ያ ነገር በጊዜ ሂደት ውስጥ ተመልሶ አለመምጣቱን ማረጋገጥ አለበት ። ሌላው ለአንድ መሪ እንቅፋት የሚሆነው መልካም ስሙን መጠበቅ ካልቻለ ነው ። አለማችን በታሪክ ስማቸውን ባለመጠበቃቸው ለውድቀት የተዳረጉ በርካታ መሪዎችን አስተናግዳለች ።
አንድ መሪ ችግሮች ገና ብቅ ሲሉ መለየት ካልቻለ ፣ የመሪነት ብቃት እንደሚጎድለው ሊገመት ይችላል ። ነገር ግን ይህ ክህሎት በብዙ መሪዎች ዘንድ ጎድሎ የሚገኝ ብቃት ነው ። አንድ ችግር ገና ሲፈጠር አውቆ ችግሩን ማስተካከል ቀላል ሲሆን ፣ በአንፃሩ መለየቱ ግን ከበድ ይላል ። ነገር ግን ያ ችግር አድጎ እና ጎልምሶ በቀላሉ በማንም ሰው ሊታይ የሚችልበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ፣ ማስተካከል አዳጋች ይሆናል ። ልክ አንድ በሽታን ሀኪም ሲጀምር ህመምተኛውም ሆነ ሀኪሙ በቀላሉ ለመለየት እንደ ሚያስቸግራቸው ነገር ግን በሽታው ቢታወቅ ግን ማከም ቀላል እንደሆው ሁሉ ፣ በሽታው ከተንሰራፋና ከተስፋፋ በኋላ ግን ሀኪሙና ህመምተኛው ብቻ ሳይሆኑ ማንም ሰው በቀላሉ የሚያየው ይሆናል ፣ለማዳን ግን ጊዜው ረፍዷል -የማይድንበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ልዩነቶችንም መጠበቅ እንዲሁ አስፈላጊ ሲሆን ፣ ለምሳሌ በእንግሊዝ ሀገር የሌበር ፓርቲው ምንም እንኳን ግራ ዘመም ቢሆንም ፣ ነገር ግን የወሰዳቸው እርምጃዎች ለምሳሌለንደንን የፋይናንስ ማእከል ማድረጉና ፣ በርካታ የወግ አጥባቂዎቹንም ርእዮተ – አለም በመውሰድ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ በሁለቱ ፓርቲዎች መሀከል ያለውን ልዩነትን አጥቧል ። ሌላውም እንዲሁ በአሜሪካን አገር ምንም እንኳን ሁለቱም ፓርቲዎች ዲሞክራቶችም ሆኑ ሪፐብሊካኖች አንዱ ስልጣን ሲይዝ አንዱ ሲቃወም የተለየ መስሎ ለመራጩ ቢታይም በተግባር ግን አዲሶቹ መሪዎች ከቀድሞው ፖሊሲ አለመከተላቸው መሪ የተለየ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ታይቷል ። ጉልህ የሆነ ልዩነት በሁለቱ መሀከል የሚታየው በግብርን መጨመርና አለመጨመር ጉዳይ ላይ ሲሆን በሌሎች ጉዳዮች ላይ ግን የሚጠበቀው ልዩነት በተግባር አይታይም ። ቀድሞ ቡሽ አሸባሪዎችን በጓንታናሞ ቤይ ሲያስሩ ፣ የቡሽን ድርጊቶች ነቅፈው ወደ ስልጣን የመጡት ኦባማ ደግሞ በስልጣን ዘመናቸው ፣አሻባሪዎች ናቸው የሚሏቸውን በሰው አልባ አውሮፕላኖች መግደልን አማራጭ አድርገው ወስደውት ቆይተዋል ። ስለዚህ ሁለቱም አስተዳደሮች በቅርፅ ጦርነት ውስጥ ይበልጥ እየተዘፈቁ መጡ እንጂ ከጦርነት ራስን የማውጣትና ሌላ አቅጣጫን የመያዝ አዝማሚያ አላሳዩም ። ይህም በሁለቱ ፓርቲዎች መሀከል በዚህ ዘርፍ ልዩነት የሚል አስተሳሰብን በመራጩ ህዝብ ዘንድ እንዲያድርና ሁለቱንም አንድ አድርጎ እንዲያያቸው ያደርጋል ለመራጩ ህዝብም አማራጭን ያሳጣል ።
ይህ ብቻ ሳይሆን ለድርድር ክፍት የሆኑ ስርአቶች በአጭር ጊዜ በድርድሩ የተወሰነ ስልጣናቸው ሊቀነስ ቢችልም እና የፖሊሲ ለውጥን ወይም ማሻሻያን እንዲያደርጉ ቢገደዱም ፣ ውሎ አድሮ ግን በድርድር ያጣውን መልሶ ለማግኘት ይችላል ። ለድርድር ክፍት ያልሆኑ ስርአቶች ግን ምንም እንኳን ለድርድር (Compromising) ፈቃደኛ ስለማይሆኑ ለወቅቱ ምንም ስልጣናቸው ባይቀነስና የፖሊሲ ማሻሻያን ወይም ለጊዜው ለውጥን ባያደርጉም ፣ ውሎ አድሮ ግን ነባር ችግሮችና ልዩነቶች ጉልበት ጨምረው ይመጡባቸዋል ። ይህ ብቻ ሳይሆን ሙሉ ሽግግር የሚደረግበት ሁኔታ ከተፈጠረ ፣ቀድሞ ነገሮች በተወሰነ ደረጃ የለዘቡ ስለሚሆን ሽግግሩን ቀላል ሲያደርግ እንደ አብዮት የመሳሰሉ ስር ነቅል የስርአት ለውጦችን ከማድረግ ያድናል ።
አንድ መሪ የሚያደርገውን ነገር የሚያስከትለውንም ሆነ ያሚያደርገውን ነገር መዘዙንም ሆነ ጠንቁን ክፉንናደጉን በሚገባ የሚረዳ ነው መሆን አለበት ። ይህም ንቃተ – ህሊናው (Consciousness) ሊኖረው ሲገባ ነው ። ንቃተ – ህሊና ማለት አሁን እሚደረግ ነገር በወደፊቱ ላይ በራሱም ሆነ በሌሎች ላይ ያለውን አንድምታ በበጎም ይሁን መጥፎ ከሌሎችበተሻለ መረዳት መቻል እንዲሁም ፣ በሌላ አነጋገር ንቃተ – ህሊና ማለት ሌሎችንም ሆነ ራስን በሚገባ ማወቅ (Self – Consciousness) ማለት ነው ።አንድ ሰው ራሱ በሌሎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ መረዳት ፣ እንዲሁም ሌሎች በሱ ላይ የሚኖራቸውን ተፅእኖ በአግባቡ መረዳት ራስን ለማወቅ በእጅጉ ይረዳል ። ራስን ማወቅ ማለት በተዘዋዋሪ መንገድ ሌሎችን ጠንቅቆ መረዳት ማለት በመሆኑ ፣ ራሳቸውን ሆነ ሌሎችን ጠንቅቀው የሚያውቁ መሪዎች የተሻሉ ውጤታማ መሪዎች መሆናቸው በአስተዳደር ባለሙያዎች በተደጋጋሚ የታረጋገጠ ነገር ነው ።
በሰው ልጅ ዘንድ ሁለት አይነት ህሊናዊ ንቃቶች አሉ ተብሎ ይታመናል ። አንደኛው አእምሯዊ – ንቃተ – ህሊና (Mind Consciousness) የሚባለው ሲሆን ። ይህ ህሊናዊ ንቃት አለምን በየቀኑ የሚመራና የሚያስተዳድር ምክንያታዊ በሆነው የአእምሮ ክፍል የሚመራ ነው ። ይህም በአብዛኛው በዘመናዊ ትምህረት የሚሰጥና የተለያዩ ሙያዎችም ማለትም ምጣኔ – ሀብትን ፣ ፖለቲካን ፣ ሳይንስን ፣ስፖርት ፣ ስነ – ጥብብን ወዘተ የሚመራ ነው ። ይህም በትምህርት ስርአቱ ውስጥ የሚሰጥና በአለም ዙሪያ ባሉ ሀገራት በሙሉ ትምህርት መልክ የሚሰጥ ነው ።
ሌላኛው ሁለተኛው እንዲሁም የበለጠው መንፈሳዊ ህሊናዊ ንቃት (Spritual Consciousness) ነው ። ይህ በአብዛኛው በሀይማኖት መስራቾችና በሀይማኖት ሰዎች የሚታወቅ ነው ። መንፈሳዊ መገለጥ ተደርጎም ሊወሰድ ይችላል ። በአለም ላይ ታላላቅ ሀይማኖቶችን የመሰረቱ ሰዎች የዚህ ህሊናዊ ንቃት ባለቤቶች የነበሩ ናቸው ።እነኚህ መንፈሳውያን «ሚስቲክ» የሚባሉ ናቸው ። በየትኛውም ዘመን ግን የዚህ አይንት ሰዎች ቁጥራቸው ብዙም አይደለም ። በብዙ ክፍለ – ዘመናት ውስጥ ፣ ለሰዎች ብርሀን ለመሆን አንድ ጊዜ የሚከሰቱ ክስተቶች ናቸው ። ቡድሀ ፣ ክርስቶስ ፣ ሙሴ፣ ባሁላን የመሳሰሉ ሰዎች የዚህ የሚጠቀሱ ናቸው ። የዚህ አይነቱ ህሊናዊ – ንቃት የንቃት ከፍተኛው ደረጃ ሲሆን የዚህ አይነት ህሊናዊ – ንቃት ላይ ለመድረስ እዝነት (Compassion) እንዲሁም አለምን እንዳለችው መቀበል መቻልን ፣ ለመለወጥ አለመታገል እንዲሁም ያለውን ነባራዊውን ሁኔታ መቀበል (Surrender) ማለት ነው ። ይህም በምክንያት የተሞላው አእመሯዊ ከሆነው ህሊናዊ ንቃት በእጅጉ የተለየ ነው ። ለምሳሌ በአንድ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ሰውንና አንድ የሀይማኖት ሰውን ብንጠይቅ ሁለቱ የሚሰጡት መልሶች የተለያዩ ናቸው ። በአሁኑ ወቅት የአለም የፖለቲካ መሪዎች ህሊናዊ ንቃት እንዲኖራቸው ይመከራል ። ይህም ለአለም ሰላም አስፈላጊ ጉዳይ ስለሆነና
ለምሳሌ መሪው በሚመራው ክፍል ውስጥ አንድ ችግር ቢፈጠር ለምሳሌ አንዱን ምንም ስህተት መስራት የለበትም ቢባል ፣ ወይንም አንዱ የሰራውን ስህተት አንደኛው አጉልቶ ቢያይበት ሰውየው ካደረገው በላይ እንዲቀጣ ቢፈልግ የፖለቲካ ችግር ተፈጥሯል ማለት ነው ። ይህም እስከ ፍርድ ቤት ድረስ መካሰስ ደረጃ የሚያዳርስ ሲሆን ፣ ይህም የፖለቲካ ወይም የህግ ችግር ተፈጥሯል ማለት ነው ፣ ይህም ጠለቅ ያለ የመረዳት ችሎታን ይጠይቃል ። ይህም ማለት ጉዳዩ በፖለቲካ ወይንም በህግ መታየት ያለበትና በዛ መንገድ ብቻ መፍትሄን የሚፈልግ ነውማለት ነው ።
ሌላው መሪነትን ቀውስ እሚያስከትል ነገር መሪው በስሩ የሚመራአቸው ተቋማት ከእርሱ ስልጣንና ቁጥጥር ወሰን ውጪ መሆን የሌለባቸው ሲሆን ፣ የአንዱ ተቋም ስልጣን ወሰን ከሌላኛው በግልፅ የተለየ መሆን አለበት። በአሜሪካ ለምሳሌ ሲአይ ኤንና ኤፍ ቢ አይን የስልጣን ወሰን በመለየት አሻሚ እንዳይሆን ማድረግ ችለዋል ። የዚህ አይነት ግልፅ የሆነ የስልጣን ወሰን ከሌለ አንድ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት የሚጠየቅ ስለማይኖር አንዱ በአንዱ ላይ ጣቱን እንዲጠቁም እና በአንድ ተቋም (መንግስት) ውስጥ ለአንድ አላማ የሚሰሩ ተቋማት መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር ያደርጋል ፣ሌላው ደግሞ መሪው በስሩ በአግባቡ ሊመራቸው ይገቡ የነበሩትን ሰዎችን ወይንም ተቋማትን በአግባቡ መምራት ካልቻለ ስርአት አልበኝነት ወይንም (Anarchy) ይፈጠራል ። ስርአት አልበኝነት በዘርፉ ባለሙያዎች በጣም የሚፈራ እና እንዳይከሰት በጥብቅ ጥረት የሚደረግበት ሲሆን መሪም ይህንን ሊፈጠር የሚችል ስርአት አልበኝነት አጥብቆ መከላከል አለበት ። ባሀኡላ እንደሚለው « እውቀቱ ለሌለው ሰው ነፃነትን ከመስጠት በላይ የበለጠ አደገኛ ነገር የለም» ።
ይህ አባባል በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ እየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ለማስተማር ከተናገረው በመዋስ ፣ የተከፋፈለ ቤት አይቆምም እንዲል መፅሀፉ ፤ ይህንን አባባል አብረሀም ሊንከን በአሜሪካን አገር ሰሜኑ ከባርነት ነፃ በሆነበትና ደቡቡ የአሜሪካ ክፍል ከባርነት ነፃ በነበረበት ወቅት ማለትም በአንድ ሀገር ላይ ሁለት ስርአትና ህግ በነበረበት ወቅት ይህን አባባል ተጠቅሞበታል ።እየሱስ ክርስቶስም እንዲሁ አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች መታዘዝ አይችልም ሲል አንድ ሰው ለሁለት አለቆች በአንድ ጊዜ ሊያገለግል አይችልም ማለት ነው ። አንድ መሪ ከሁለት አለቆች ትእዛዝን እሚቀበልበት ሁኔታ ሲፈጠር ቦታውን እልቀበልም ቢል ይመረጣል የሚል አስተሳሰብ አለ ።
ሌላው ደግሞ መሪዎች ነገሮችን መቆጣጠር ሲያቅታቸው ፣ ወይንም በአግባቡ መምራት ሲያስቸግራቸው ወይንም አመፅ ሲያጋጥማቸው በሽብር (Terror) ለመምራት ሊሞክሩ ይችላሉ ።ነገር ግን ይህ ስልት ለአጭር ጊዜ ሊሰራ ቢችልም በረጅም ጊዜ ግን ስኬታማነቱ እየቀነሰ ስለሚሄድ አዋጪ ስልት አይደለም ፣ውሎ አድሮ በመሪው ላይ ተቃራኒ ውጤትን ማስከተሉም አይቀሬ ነው ። ይህ ብቻ ሳይሆን ጎጂናበረጅም ጊዜ በቀላሉ የማይስተካከል ከባድ ዋጋንና ጥፋትን የሚያስከትል ሆኖ ሊገኝ ይችላል ። እንዲሁም የመሪዎቹን በታሪክ ትተውት በሚያልፉት አሻራ ላይ ጥቁር ነጥብን ጥሎ ያልፋል ።
በመሪነት ውስጥ የመሪነትን ቀውስን ከሚያስከትሉ ነገሮች አንዱ የበላይ አመራር እርስ በእርስ መከፋፈል ነው ። ሌላው ደግሞ የአመራር መፈረካከስ ነው ። አንድ አመራር በራሱ ውስጣዊ ችግር ምክንያት ሊፈረካከስ ይችላል ። ለምሳሌ እርስ በእርሱ ከተከፋፈለና ያንን ልዩነቱን በውይይት መፍታት ካልቻለ ፣ እንዲሁም ለምሳሌ መሪው ቢታመምና መምራት ቢያቅተውና አግባብ ባለው መንገድ አዲስ አመራርን መተካት ካልቻለ ፣ እንዲሁም የመሪው ማርጀት ፣መጃጀትና እንዲሁም በአዲስ ለመተካት ፈቃደኛ በማይሆንበት ወቅት የአመራር መፈረካከስ ሲፈጠር እንዲሁም ይህ በበኩሉ የአመራር እና የስልጣን ክፍተትን ይፈጥራል ። ይህ የስልጣን ክፍተትን የስልጣን ሽኩቻንና የአመራር አቅጣጫ መሳትንና መዋለልን ያስከትላል ።
ሌላው ለመሪነት ቀውስ አስተዋፅኦ የሚያደርገው ነገር ፣ መሪው የሚመራበት ዘመን ራሱ ይወስነዋል ። ለምሳሌ የሰላም ዘመን መሪ ፣ ለጦርነት ጊዜ ላይሆን ይችላል ። የጦርነት ጊዜ መሪ ደግሞ የሰላም ዘመን መሪ ላይሆን ይችላል ።ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሆኑት ዊኒስተን ቸርችል ሲሆኑ እንግሊዝን ከናዚ መንጋጋ ማዳን ቢችሉም በሰላሙ ጊዜ ግን በምርጫ ተሸንፈዋል ። በእርግጥ መራጩን ህዝብ ውለታ ቢስ ስለሆነ ሳይሆን በጦርነት ጊዜ አንድ መሪ የተከተለው ስረትራቴጂና በሰላም ወይም ትልቅ ችግር በሌለበት ሰአት የሚኖረው የአመራር ስልት የተለያየ ስለሆነና መሪው ራሱን ለሁኔታዎች ጋር ካለማዛመድና ካለመረዳት የሚመነጭ ነው ።
እንዲሁም ፈረንሳይን ከናዚዎች በጀግንነት ተዋግተው ነፃ ያወጡት ቻርልስ ደጎልም ፈረንሳይን ነፃ ካወጡ በኋላ በፊት በጦርነቱ ሰአት እንደነበራቸው ተወዳጅነታቸውን ጠብቀው አልዘለቁም ፤ ብዙም ተወዳጅ አልነበሩም ።ደጎልም እንደ ቸርችል ሀሉ በምርጫ ተሸንፈዋል ።
በመሪነት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የህልውና ጉዳይን ለመረዳት በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ሩዝቬልት እንዲሁም ቸርችል የእንግሊዝ መሪዎች ባይሆኑ ኖሮ አሜሪካ በኮሚኒስቶች ወይንም በፋሺስቶች እጅ ውስጥ መግባቷ አይቀርም ነበረ ፣ አውሮፓም የናዚ ጀርመን መፈንጫ ልትሆን ትችል ነበረ ፣ በእንደዛ ሁኔታም ናዚዎችን ከአለም ላይ ማጥፋት አይቻልም ነበረ ማለት ይቻላል የሚሉ የታሪክ ሰዎች አሉ ፤ ይህም መሪዎች ምንያህል የታሪክን አቅጣጫ በበጎም ይሁን በመጥፎ ሊቀይሩ እንደሚችሉ የሚያመለክት ነው።
ይህ ብቻ ሳይሆን በአብዮት ጊዜና በሰላም ጊዜም የመሪዎች ስራ ይለያያል ። የአብዮት ጊዜ መሪዎች የሰላም ጊዜ መሪዎች ሆነው ላይገኙ ይችላሉ ።
ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት የሰው ልጅ አእምሮ ጥሩ ጥሩውን ነው እንጂ አሉታዊ ወይም ክፉ የሆነውን ነገር ወደ ውስጥ አያስገባውም ያወጣዋል የሚል ግኝት አግኝተዋል ። ማለትም አንድ ሰው ጥሩ ጥሩውን ብቻ ነው እንጂ ክፉውን ወይም አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን መስማት ወይም ማየት ወይም ቢያየውና ቢሰማውም፣ እንዳለ አድርጎ ግን እውቅና መስጠትን አይፈልግም ። ይህም የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው ፣ ሁሉንም ነገሮች መጥፎ አድርጎ መመልከት ለሰዎች በጣም አሰልቺና የማይፈለግ ስለሆነ ነው ። መሪም ይህን መረዳት እውነታዊውና ነባራዊ የሆኑ ነገሮችን ለመረዳት ሊጋርደው የሚችለውን ነገር ለመረዳት ሊያግዘው ይችላል ።
ሌላው አንድ መሪ ራሱን ተፈላጊ ማድረግ በረጅም ጊዜ አንዱን ሀላፊነት ከጨረሰ በኋላ ሌሎች የበላለጡ እድሎች እንዲከፈቱለት ያደርጋል ይህም የሚሆነው መልካም ስሙንና ተአማኒነቱን የጠበቀ መሪ ከሆነ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ተፈላጊ ያደርገዋል ።መልካም ስም ውስጥ ክተተው ።የመሪነት ቀውስ (Leadership Crisis)

ሌላው አንድ መሪ ራሱን ተፈላጊ ማድረግ በረጅም ጊዜ አንዱን ሀላፊነት ከጨረሰ በኋላ ሌሎች የበላለጡ እድሎች እንዲከፈቱለት ያደርጋል ይህም የሚሆነው መልካም ስሙንና ተአማኒነቱን የጠበቀ መሪ ከሆነ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ተፈላጊ ያደርገዋል ።መልካም ስም ውስጥ ክተተው ።eadership Crisis)

ሌላው አንድ መሪ ራሱን ተፈላጊ ማድረግ በረጅም ጊዜ አንዱን ሀላፊነት ከጨረሰ በኋላ ሌሎች የበላለጡ እድሎች እንዲከፈቱለት ያደርጋል ይህም የሚሆነው መልካም ስሙንና ተአማኒነቱን የጠበቀ መሪ ከሆነ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ተፈላጊ ያደርገዋል ።መልካም ስም ውስጥ ክተተው ።

ልዩነቶቻችን ውበታችን የሚሆኑት ስናስተናግዳቸው ብቻ ነው፤
አለበለዚያ ያወዛግቡናል ። (አርቲክል 2012)