የራሱ ልዩ ወታደር ያለው ማለትም ሌሎች ክልሎች ካላቸው የተለየ military force ያለው ክልል ትግራይ ብቻ ነው ።ህወሀት ከስምንት ሺ ጦር በላይ አስፍሮ የአማራ ክልልን በመድፈር ወጣቶችን እያፈሰ እና እየገደለ እንዳለ የአለም ዜና አውታሮች ሳይቀር እየዘገቡት ነው።

ሆኖም የህወሀት እብሪት ዛሬም ባለመሰልጠን ጉዞበማታለል ላይ መሆኑ ይደንቃል።የህወሀት ወታደሮች ህዝብ እየገደሉ መሆኑን ያገሪቱ ቴሌቭዥን ሲዘግብ እንኩዋን ውሸት ነው በማለት አጣጣለው።

የዶክተር አብይን መንግስት ድጋሜ መተን እንይዘዋለን ትንሽ እራሳችን ገለል ብለን እንየው ብለን ነው በሚል በግልፅ የተናገሩትን የህወሀት ወታደሮች ዛቻ ሰምተናል።የአብይን መንግስት አይደለም ያሰበውን ምን ሊያስብ እንደሚችል የዝንብ ጠንጋራን መለየት እንደማይሳናቸው የነገሩን ደብረ ፂወን ናቸው።

አሁን ሌላውን አሉቡዋልታ እንተወውና ለሁሉም ሚዛናዊ የሆነውን እውነት ባይናችን ያየነውን ከአገር ውስጥ እስከ አለም አቀፍ ዜና አውታሮች ያሳዩንን እውነት እንጋፈጠው ።
ከህወሀት እና አዴፓን እጅግ ሲበዛ በሰለጠነ መንገድ ትግስት ያሳየው ማን ነው ከተባለ አዴፓ ነው።

አዴፓ በዚህ ጉዳይ በወሰደው አቁዋም ሊደነቅ ይገባል ከስምንት ሺ ጦር በላይ የአማራ ክልል ድንበር ላይ ሳይቀር አስፍሮ ሰው እየገደለ ያየነው ህወሀትን መሆኑን ያገሪቱ ቴሌቪዥን ሳይቀር ነግሮናል ከስፍራውም ሄደን አረጋግጠናል።

አዴፓ እስካሁን የወሰደው እርምጃም ሆነ እንደ ህወሀት ታጣቂ ወደ ድንበር አላሰፈረም በህግ እና ፌደራል ስርአቱ በሚጠይቀው እንዳኝ ሲል ነው ያሳሰበው።ሆኖም ህወሀት ይህን ሁሉ ወሬ ገደል ከቶ በአማራ አፋር እና ጋምቤላ ሳይቀር ወረራ እና ግድያ ፈፀመ።

በተለይ ባለፉት ሶስት ቀናት ያደረገው ተግባር የአብይን መንግስት ሙሉ ለሙሉ እውቅና ነፍጎ ምን ታመጣለህ የሚል ወረራ ነው።የአፋር እና አማራ ክልል ህዝቦችያደረጉት ፍፁም ሰላማዊ ነው እብሪተኛው ህወሀትን መንገድ በመዝጋት ግንኙነት ማቆም ።

በተለት በአማራ ክልል የተደረገበት ማዕቀብ በቃላት ሚገለፅ አልሆነም 60% የህወሀት ኢኮኖሚ የሚመነጨው ከአማራ ክልል ነው ይህ በመዘጋቱ በትግራይ የሚገኙ ፋብሪካወች ሳይቀር አንጋጠው ሰማይ ጠባቂ ሆኑ።

የአማራ ህዝብ በሰላም ከገዳዩ ተለየ ከዚህ የበለጠስልጣኔ የለም ህወሀት ግን እንደገና ለምን በሚል የኢኮኖሚው ማዕቀብ ግፊትን ለመቀነስ በሰላም ከአዴፓ ጋር ድርድር ከማድረግ ይልቅ ባልሰለጠነ መልኩ የወታደር ወረራውን ተያያዘው።

እራሱ ወሮ እራሱ ገሎ በሰላም ምንም ሳያደርጉ በቃን ብለው መንገዳቸውን ዘግተው በተለዩት የአፋር እና የአማራ ህዝብ ላይ ይበልጥ ጦሩን በማዝመት ለክስ ሲሩዋሩዋጥ ብዙወች ምን አይነት ስብስብ ነው ህወሀት እንዲሉ አርጎዋቸዋል።አሁን ጥያቄው ከበድ ብሎዋል የህወሀትን ህገወጥ ወረራ ከዚህ በላይ የአፋር ህዝብ እና የአማራ ህዝብ የሚታገሱት አልሆነም ።

ትልቅ እድል የሰጡት ህወሀት እብሪቱ ከፍ ብሎ ከግዛት ወሰኑ አልፎ በሶስት ክልሎች ግድያ እና ወረራ እየፈፀመ ነው።የአፋር ህዝብ መንገዱን ከመዝጋት አልፎ ዝምብለን አንሞትም በሚል የደፈጣ ውጊያ ውስጥ ከገባ ሰንብቱዋል።

እጅግ ሲበዛ ትግስተኛው አዴፓ ይህን ሁሉ ወረራ እየፈፀመ ለፌደራል መንግስቱ ጉዳዩን ወደሌላ አቅጣጫ ከመሄዱ በፊት በሰላም ጠይቁዋል። የፌደራል መንግስቱ ይህን ካላስቆመ ግን አዴፓ ዝም ብሎ እንዲያይ የክልሉ ህዝብ አይፈቅድለትም ።

የአማራ ህዝቦች ላሳያችሁት ትልቅ ትግስት ያለኝን አክብሮት እገልፃለሁ ባለፈው ሳምንት 7 ሰው ገሎ 30 አቁስሎ እና በክልላችሁ ገብቶ ወጣቶችን አፍሶ ወስዶ ሰላም ይሻላል ብላችሁ መንገድ ብቻ መዝጋታችሁ ትልቅ ስልጣኔ ነው ።

አዴፓ ትግስቱ ሰፊ መሆኑን አስመስክሩዋል ሲበዛ ሰፊ ትግስት ጦርነት ማንንም አይጠቅምም በሶስቱ ክልሎች ጦርነት ተነሳ ማለት እስከመጨረሻው ተለያዩ ማለት ነው የፌደራል መንግስቱ ዝምታ ክልሎቹ እርስ በእርስ ጦርነት ሲገቡ ዝም ለማለት ከሆነ ፌደራልነቱን ያፍርሰውና እራሳቸው ይወጡት ።ከዚህ ባለፈ ግን ምንም ሳያጠፉ በራሳቸው ክልል በህወሀት ወታደር ንፁሀን ህዝቦች መገደል የለባቸውም።

የህወሀት መንግስት ትልቁ እብሪት የሰው ክልል ወሮ እየገደለ በፌደራል መንግስቱ ላይ ምንም አታመጣም ብሎ ማቅራራቱ ብቻ አይደለም በሰላም መንገዳቸውን በዘጉት ላይ ዘልቆ ገብቶ ጦርነት መፍጠሩ ነው።

የአብይ መንግስት ትግስት እስከምን ድረስ ነው የሚለውን የብሎንበርግ ጋዜጠኛ በስፍራው ያየውን ሲዘግብ” የአንድ አገር መንግስት ባለበት የክልል ጦር ሌላ ክልል ወሮ ይህን ግፍ ሲፈፅም ዝም ማለቱ ለምንድነው?? ብዙ ህዝብ ተገሉዋል በተለይ የአማራ እና የአፋር ህዝብ ” በሚል የፌደራል መንግስቱን ቸልታ ወርፎታል ።

የአፋርም የአማራ ህዝብም በሚገባ ለፌደራል መንግስቱም ለአለምም ሰላም ወዳድነታቸውን በሚገባ አሳይተዋል ነገር ግን የፌደራል መንግስቱ ዝምታ እና ባላየ ማለፍ በዚህ ከቀጠለ እራሳቸውን የመከላከል የተፈጥሮ ግዴታቸው ነው።

በሰላም ተግባብቶ እና ተከባብሮ መኖር ለሁሉም ይበጃል ጦርነት ከመገዳደል የዘለለ የህዝቦችን እስከወዲያኛው መለያየትን ያመጣል።

ከህወሀት የቀድሞ መስራቾች መሀል ሁለቱ በቅርብ ቀናት የህወሀትን መነሻ እቅድ በማጋለጥ ከአፋር እና ከአማራ ህዝብ ላይ የወሰዳቸው መሬቶች በሙሉ በወረራ እንጅ የህወሀት እንዳልሆኑ አጋልጠዋል።

Leave a comment